የጥናት እርዳታዎች
ሞሮኒ፣ የሞርሞን ልጅ


ሞሮኒ፣ የሞርሞን ልጅ

በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ የመጨረሻው የኔፋውያን ነቢይ (በ፬፻፳፩ ዓ.ም. አካባቢ)። ከሞርሞን ሞት በፊት፣ የሞርሞን ሰሌዳዎች ተብለው የሚጠሩትን የታሪክ መዝገቦች ለልጁ ሞሮኒ ሰጠ (ቃላት ፩፥፩)። ሞሮኒ የሞርሞን ሰሌዳዎችን ማዘጋጀትን ጨረሰ። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ምዕራፍ ፰ እና ፱ን ጨመረ (ሞር. ፰፥፩)። መፅሐፈ ኤተርን አሳጥሮ ጻፋቸውና ጨመራቸው (ኤተር ፩፥፩–፪) እናም መፅሐፈ ሞርሞን የሚባለውን የእርሱን መፅሐፍ ጨመረ (ሞሮኒ ፩)። ሞሮኒ ሰሌዳዎችን አተመ እና በከሞራ ኮረብታ ውስጥ ደበቃቸው (ሞር. ፰፥፲፬ሞሮኒ ፲፥፪)። በ፲፰፻፳፫ (እ.አ.አ.) ሞሮኒ ከሞት እንደተነሳ ሰው መፅሐፈ ሞርሞንን ለጆሴፍ ስሚዝ እንዲገልፅ ትልኮ ነበር። (ት. እና ቃ. ፳፯፥፭ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴–፵፪፣ ፵፭)። ወጣቱን ነቢይ ከ፲፰፻፳፫ እስከ ፲፰፻፳፯ (እ.አ.አ.) አስተማረው (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፶፬) እና በመጨረሻም በ፲፰፻፳፯ (እ.አ.አ.) ሰሌዳዎችን ለእርሱ ሰጠው (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፶፱)። መተርጎምን ከጨረሰ በኋላ ጆሴፍ ስሚዝ ሰሌዳዎችን ለሞሮኒ መለሰ።

መፅሐፈ ሞሮኒ

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የመጨረሻው መፅሐፍ። የተጻፈው በኔፋውያን የመጨረሻ ነቢይ ሞሮኒ ነበር። ምዕራፍ ፩–፫ ስለኔፋውያን የመጨረሻ መደምሰስ ይናገራሉ፣ መንፈስ ቅዱስን እና ክህነትን ስለመስጠት መመሪያ ይሰጣሉ። ምዕራፍ ፬–፭ የቅዱስ ቁርባንን ማስተዳደር ዘዴን ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፮ የቤተክርስቲያኗን ስራ በማጠቃላል ይገልጻል። ምዕራፍ ፯–፰ ከሞርሞን የእምነት፣ ተስፋና፣ ልግስና ትምህርት እና ጥሩን ከመጥፎ ስለመፍረድ መንገድ በተጨማሪ የወንጌልን ቀዳሚ መሰረታዊ መርሆች (ሞሮኒ ፯)፣ እናም ትንሽ ልጆች በክርስቶስ ህያው የሆኑና ጥምቀት እንደማያስፈልጋቸው ሞሮኒ የገለጸበት (ሞሮኒ ፰) ስብከቶች ናቸው። ምዕራፍ ፱ የኔፋውያን ህዝቦች በስነምግባር የጎደለ እንደነበረ ይገልጻል። ምዕራፍ ፲ የሞሮኒ የመጨረሻ መልእክት ነው እናም በተጨማሪ መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ የሚታወቅበትን መንገድ ይገልጻል (ሞሮኒ ፲፥፫–፭)።