የጥናት እርዳታዎች
ምናሴ


ምናሴ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የአስናት እና ወደ ግብፅ የተሸጠው ዮሴፍ ታላቅ ልጅ (ዘፍጥ. ፵፩፥፶–፶፩)። እርሱና ወንድሙ ኤፍሬም የያዕቆብ (የእስራኤል) የልጅ ልጆች ነበሩ ነገር ግን እነርሱ የእርሱ አደረጋቸው እናም ልክ እንደ እርሱ ልጆች እንደሆኑ ባረካቸው (ዘፍጥ. ፵፰፥፩–፳)።

የምናሴ ጎሳ

የምናሴ ትውልዶች ከእስራኤል ጎሳዎች መካከል የተቆጠሩ ነበሩ (ዘኁል. ፩፥፴፬–፴፭ኢያ. ፲፫፥፳፱–፴፩)። ደግሞም ለኤፍሬምና ለምናሴ ተሰጥቶ የነበረው ለዮሴፍ ጎሳ የተሰጠው የሙሴ በረከት በኦሪት ዘዳግም ፴፫፥፲፫–፲፯ ውስጥ ተመዝግቧል። የተመደበላቸው ምድር ከዮርዳኖስ ወደ ምዕራብ በኩልና ከኤፍሬም አጠገብ ነበር። በዮርዳኖስ ምስራቅ በበሳን እና በገለዓድ ጥሩ የግጦሽ መሬት ውስጥም ሰፍረው ነበር። በመጨረሻው ቀናት፣ የምናሴ ጎሳ የኤፍሬም ጎሳን የተበተኑትን እስራኤል በመሰብሰብ ይረዳሉ (ዘዳግ. ፴፫፥፲፫–፲፯)። የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ ሌሂ የምናሴ ትውልድ ነበር (አልማ ፲፥፫)።