የጥናት እርዳታዎች
ሚልክያስ


ሚልክያስ

በ፬፻፴ ም.ዓ. አካባቢ የጻፈና የተነበየ የብሉይ ኪዳን ነቢይ።

ትንቢተ ሚልክያስ

የሚልክያስ መፅሐፍ ወይም ትንቢት የብሉይ ኪዳን የመጨረሻ መፅሐፍ ነው። ይህም የሚቀጥሉት አራት ጭብጥ መልእክቶች ነበሩት፥ (፩) የእስራኤል ኃጢያቶች—ሚልክያስ ፩፥፮–፪፥፲፯፫፥፰–፱፤ (፪) ታዛዥ ባለመሆናቸው ምክንያት በእስራኤል ላይ የሚመጣው ፍርድ—ሚልክያስ ፩፥፲፬፪፥፪–፫፣ ፲፪፫፥፭፤ (፫)፤ ለታዛዥነት ቃል ኪዳን—ሚልክያስ ፫፥፲–፲፪፣ ፲፮–፲፰፬፥፪–፫፤ እና (፬) እስራኤልን በሚመለከት ትንቢቶች ሚልክያስ ፫፥፩–፭፬፥፩፣ ፭–፮ (ት. እና ቃ. ፪፻፳፰፥፲፯ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፯–፴፱)።

በትንቢቶቹ ውስጥ፣ ሚልክያስ ስለመጥምቁ ዮሐንስ (ሚል. ፫፥፩ማቴ. ፲፩፥፲)፣ ስለአስራት ህግ (ሚል. ፫፥፯–፲፪)፣ ስለጌታ ዳግም ምፅዓት (ሚል. ፬፥፭)፣ እናም ስለኤልያስ መመለስ (ሚል. ፬፥፭–፮ት. እና ቃ. ፪፻፳፰፥፲፯ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፯–፴፱) ጻፈ። አዳኝ የሚልክያስን ምዕራፍ ፫ እና ፬ ለኔፋውያን ጠቀሰ (፫ ኔፊ ፳፬–፳፭)።