የጥናት እርዳታዎች
የሰንበት ቀን


የሰንበት ቀን

ለእረፍት እና ለማምለክ የተመደበ ቅዱስ ቀን እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች ከፈጠረ በኋላ፣ በሰባተኛው ቀን አረፈ እናም ሰዎች እርሱን እንዲያስታውሱ በሳምንት አንድ ቀን የእረፍት ቀን እንዲሆን አዘዘ (ዘፀአ. ፳፥፰–፲፩)።

ከክርስቶስ ትንሳኤ በፊት፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት፣ አይሁዶች እንደሚያደርጉት፣ የሳምንቱን መጨረሻ ቀን እንደ ሰንበት ያከብሩ ነበር። ከትንሳኤ በኋላ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት፣ አይሁድም ይሁኑ አህዛብ፣ ስለጌታ ትንሳኤ ለማስታወስ የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን (የጌታን ቀን) ያከብራሉ። ዛሬም ቤተክርስቲያኗ በሳምንት አንድ ቀንን እንደ ቅዱስ የሰንበት ቀን ታከብራለች፣ በዚህም ቀን እግዚአብሔርን ታመልካለች እንዲሁም ከአለም ስራዎች ታርፋለች።

የሰንበት ቀን ሰዎችን በመንፈስ ስለመመገብ እና በእግዚአብሔር ታዛዥ ለመሆን ስላላቸው ሀላፊነት እንዲያስታውሱ ያደርጋል። ህዝቦች ሰንበትን በማክበር ግዴለሽ በሚሆኑበት ጊዜ፣ የህይወት ሁሉም ሁኔታዎች ይነካሉ እናም የሀይማኖት ህይወታቸውም ይበሰብሳል (ነሀ. ፲፫፥፲፭–፲፰ኤር. ፲፯፥፳፩–፳፯)።