የጥናት እርዳታዎች
አሜን


አሜን

“ይህም ይሁን” ወይም “እንዲህም ነው” ማለት ነው። አሜን የሚባለው ልባዊ ወይም የተከበረ ተቀባይነት እና ስምምነትን (ዘዳግ. ፳፯፥፲፬–፳፮) ወይም እውነትነት (፩ ነገሥ. ፩፥፴፮) ለማሳየት ነው። ዛሬ በጸሎቶች፣ በምስክርነቶች፣ እና ንግግሮች መጨራሻ ላይ፣ ጸሎትን ወይም ምልዕክትን የሰሙት ተቀባይነት እና ስምምነትን ለማሳየት በደንብ የሚሰማ አሜን ይላሉ።

በብሉይ ኪዳን ጊዜዎች፣ ሰው መሃላ ሲገባ አሜን ማለት ነበረበት (፩ ዜና ፲፮፥፯፣ ፴፭–፴፮ነሀ. ፭፥፲፪–፲፫፰፥፪–፮)። ክርስቶስ “አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር” ተብሎ ተጠርቷል (ራዕ. ፫፥፲፬)። በነቢያት ትምህርት ቤት አሜንም ደግሞ እንደ ቃል ኪዳን ምልክት አገልግሏል (ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፴፫–፻፴፭)።