የጥናት እርዳታዎች
ኦሪት ዘፀአት


ኦሪት ዘፀአት

በብሉይ ኪዳን ውስጥ እስራኤላዊያን ከግብፅ የወጡበትን የሚገልፅ በሙሴ የተጻፈ መፅሐፍ። በኦሪት ዘጸዓት ውስጥ በመጀመሪያ የተጻፉት የእስራኤል ታሪክ በሶስት ክፍሎች ለመከፋፈል ይችላሉ፥ (፩) የህዝቦቹ ለግብፅ ባሪያነት፣ (፪) በሙሴ አመራር ስር ከግብፅ የወጡበት፣ እና (፫) በሀይማኖት ህይወታቸው እና በፖለቲካ ህይወታቸው እግዚአብሔርን ለማገልገል ስለወሰኑበት።

የመጀመሪያው ክፍል፣ ዘጸአት ፩፥፩–፲፭፥፳፩፣ እስራኤል በግብፅ መጨቆንን፤ የሙሴ የመጀመሪያ ታሪክ እና ጥሪ፤ ተነቅለው መሄዳቸው እና የፋሲካ መጀመር፤ እናም ወደ ቀይ ባህር ጉዞአቸው፣ የፈርዖን ሰራዊት ጥፋት፣ እና የሙሴ የድል መዝሙር።

ሁለተኛው ክፍል፣ ምጽአት ፲፭፥፳፪–፲፰፥፳፯፣ ስለእስራኤል ቤዛነት እና ከቀይ ባህር ወደ ሲና በተጓዙበት የደረሱ ነገሮች፤ የማራ ውሀዎች መራራነት፣ ድርጭቶች እና መና መሰጠታቸው፣ የሰምበት መከበር፣ በራፊዲም የተሰጠው የተአምራት የውሀ ስጦታ፣ እና ከአማሌቂውያን ጋር የተዋጉበትን፤ ዮትር ወደሰፈሩበት መሄዱ እና ስለህዝባዊ መንግስት ስለነበረው ምክር ይናገራሉ።

ሶስተኛው ክፍል፣ ምዕራፍ ፲፱–፵፣ እስራኤል በሲና በነበራቸው የክብር ድርጊቶች ለእግዚአብሔር አገልግሎት ስለመቀደሳቸው ይናገራል። ጌታ ህዝቡን እንደ ካህናትና ቅዱስ ሀገሮች መንግስት ከፋፈላቸው፤ አስሩን ቃላት ሰጣቸው፤ እናም ስለታቦት፣ ስለእቃዎቹ፣ እና በእዚያም ውስጥ ስለማምለክ መመሪያ ሰጠ። ከእዚያም ህዝቦቹ የወርቅ ጥጃዎች በማምለክ ኃጢያት የሰሩበት ታሪክ ይቀጥላል፣ እናም በመጨረሻም የታቦት መሰራት እና ለአገልግሎቱ ዝግጅት ታሪክ አለ።