የደረት ኪስ
ቅዱስ መጻህፍቶች ሁለት አይነት የደረት ኪሶችን ጠቅሰዋል፥ (፩) የወታደር መከላከያ ልብስ ወይም ጥሩር የፊት ለፊት ክፍል። በምሳሌአዊ ሁኔታ፣ ቅዱሳን የጽድቅንም ጥሩር እራሳቸውን ከክፉ ለመጠበቅ መልበስ ይገባቸዋል (ኢሳይያስ ፶፱፥፲፯፤ ኤፌ. ፮፥፲፬)። (፪) በሙሴ ህግጋት ውስጥ ሊቀ ካህናት ይለብሱት የነበረ ልብስ (ዘፀአ. ፳፰፥፲፫–፴፤ ፴፱፥፰–፳፩)። በሊኖ የተሰራና በእንቁ ድንጋዮች የተጌጠ ነበር። አንዳንዴም ከኡሪም እና ቱሚም ጋር ተገናኝቶ ይጠቀሳል (ት. እና ቃ. ፲፯፥፩፤ ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፭፣ ፵፪፣ ፶፪)።