የጥናት እርዳታዎች
ሳሙኤል፣ የብሉይ ኪዳን ነቢይ


ሳሙኤል፣ የብሉይ ኪዳን ነቢይ

የሕልቃና እና የሐና ወንድ ልጅ፣ ሳሙኤል የተወለደው እንደ እናቱ የጸሎት መልስ ነበር (፩ ሳሙ. ፩)። በልጅነቱ በሴሎ ድንኳን ውስጥ ሊቀ ካህን በሆነው ዔሊ እንዲጠብቀው ተሰጠ (፩ ሳሙ. ፪፥፲፩፫፥፩)። ጌታ በወጣትነቱ ነቢይ እንዲሆን ጌታ ጠራው (፩ ሳሙ. ፫)። ኤሊ ከሞተ በኋላ፣ ሳሙኤል ታናቅ ነቢይ እና የእስራኤል ዳኛ ሆነ እናም ህግን ስርዓር፣ እና ደንበኛ የሀይማኖት አምልኮን በምድር ውስጥ እንዲገኝ በዳግም መለሰ (፩ ሳሙ. ፬፥፲፭–፲፰፯፥፫–፲፯)።

፩ ሳሙ. ፳፰፥፭–፳ ሳሙኤል በሳዖል ጥያቄ ምክንያት የዓይንዶር መናፍስትን የምትጠራ አንዲትን ሴት ከሞት ያመጣበትን ታሪክ የያዘ ነው። ይህም ከእግዚአብሔር የመጣ ራይይም አልነበረም፣ ምክንያቱም መናፍስትን የምትጠራ ሴት ወይም ሌላ ከመናፍስት የሚናገሩት በነቢይ ላይ ተጽእኖ ኖሯቸው በእርሱ ወይም በእርሷ ጥያቄ ሊታይ አይችልም።

የ፩ እና ፪ ሳሙኤል መፅሐፎች

በአንዳንድ መፅሐፍ ቅዱሶች ውስጥ መፅሀፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ እና ካዕል አንድ መፅሀፍ ናቸው። በሌሎች ውስጥ ሁለት መፅሀፎች ናቸው። መፅሐፎቹ ከሳሙእል መወለድ እስከ ንጉስ ዳዊት መሞት በፊት ድረስ የ፻፴ አመታት ጊዜን የሚሸፍኑ ነበሩ።

መፅሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ

ምዕራፍ ፩–፫ ጌታ የኤሊ ቤተሰብን እንደረገመና እንደቀጣ እንዲሁም ሳሙኤል ሊቀ ካህን እና ዳኛ እንዲሆን እንደጠራ ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፬–፮ የኪዳን ታቦት በፍልስጥኤም እጆች እንደወደቀ ይናገራሉ። ምዕራፍ ፯–፰ የሀሰት አማልክት እና ኃጢያተኛ ንጉስ መኖርና ሳሙኤል የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ይመዘግባሉ። ምዕራፍ ፱–፲፭ የሳዖል መንግስት እና የንጉስነቱን ግዛት ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፲፮–፴፩ የዳዊትን እና ሀይል ያገኘበትን ታሪክ ይነግራሉ—ሳሙኤል ጎልያድን የገደለውን ዳዊት ቀባ። ሳዖል ዳዊትን ጠላ፣ ነገር ግን ዳዊት ምንም እንኳን ይህን ለማድረግ እድል ቢኖረውም ሳዖልን ለመግደል ፈቃደኛ አለነበረም።

መፅሐፈ ሳሙኤል ካልዕ

ይህ መፅሐፍ የዳዊትን እንደ ይሁዳ እናም በመጨረሻ እንደ እስራኤል ሁሉ ንጉስ ዘመነ መንግስት የያዘ ነው። ምዕራፍ ፩–፬ በይሁዳ ከተዘወደ በኋላ፣ በዳዊት ተከታዮች እና በሳዖል ተከታዮች መካከል የነበረውን ትግል ያሳያሉ። ምዕራፍ ፭–፲ ዳዊት በብዙ ምድሮች ላይ ሁሉ ሀይለኛ እንደሆነ ያሳያሉ። ምዕራፍ ፲፩–፲፪ ዳዊት በኃጢያቶቹ እና በቤተሰቡ አመፅ ምክንያት መንፈሳዊ ጥንካሬው መዳከሙን ያሳያሉ። ምዕራፍ ፳፪–፳፬ ዳዊት ከጌታ ጋር ለመታረቅ የሞከረበትን ይገልጻሉ።