የጥናት እርዳታዎች
መባረክ፣ የተባረከ፣ በረከት


መባረክ፣ የተባረከ፣ በረከት

መለኮታዊ ድጋፍን ለአንድ ሰው መስጠት። ለእውነተኛ ደስታ፣ ለደህንነት፣ ወይም ለብልፅግና ተጨማሪ ምክንያት የሚሆነው ማንኛውም ነገር በረከት ነው።

በረከቶች ሁሉ በዘለአለማዊ ህግጋት ላይ የተመሰረቱ ናቸው (ት. እና ቃ. ፻፴፥፳–፳፩)። እግዚአብሔር ልጆቹ በእዚህ ህይወት ደስታን እንዲያገኙ እልስሚፈልግ (፪ ኔፊ ፪፥፳፭)፣ ለትእዛዛቱ ታዛዥነታቸው ውጤታ (ት. እና ቃ. ፹፪፥፲)፣ ለጸሎት መልስ ወይም ለክህነት ስልጣን ስነስርዓት (ት. እና ቃ. ፲፱፥፴፰፤ ፻፯፥፷፭–፷፯)፣ ወይም በጸጋው በኩል (፪ ኔፊ ፳፭፥፳፫) በረከቶችን ይሰጣቸዋል።

ክርስቶስ ስለመባረክ የተናገራቸው አረፍት ነገሮች ታዋቂ የሆኑ ስለብሩክነት መግለጫ የተዘረዘረ ነው (ማቴ. ፭፥፩–፲፪፤ ፫ ኔፊ ፲፪፥፩–፲፪)።

አጠቃላይ

ልጆችን መባረክ