የጥናት እርዳታዎች
ወደ ሮሜ መልእክት


ወደ ሮሜ መልእክት

በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ ጳውሎስ በሮሜ ላሉት ቅዱሳን የጻፈው ደብዳቤ። አደጋ ቢኖርበትም፣ ኢየሩሳሌምን ለመጎብኘት እያሰበ ነበር። በህይወቱ ካመለጠ፣ ከእዚያም በኋላ ሮሜን ለመጎብኘት ተስፋ ነበረው። ደብዳቤውን የጻፈው፣ እርሱ ሲመጣ እርሱን ለመቀበል በእዚያ ያለችው ቤተክርስቲያን እንድትዘጋጅ ነበር። ይህም ክርክር የነበረባቸውን እና አሁን ጳውሎስ በመጨረሻ ተመስርተዋል ብሎ የተመለከታቸውን የአንዳንድ ትምህርቶች መረጃ እንደያዘ ሊታይበትም ይችላል።

ምዕራፍ ፩ ጳውሎስ ለሮሜ የላከውን ሰላምታ የያዘ ነበር። ምዕራፍ ፪–፲፩ የእምነት፣ ስራዎች፣ እና ጸጋ ትምህርት ብዙ አዋጆችን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፲፪–፲፮ የፍቅር፣ የሀላፊነት፣ እና የቅዱስነት ትምህርቶችን የያዙ ናቸው።