የጥናት እርዳታዎች
መስደብ


መስደብ

ወደ እግዚአብሔር ወይም ወደ ቅዱስ ነገሮች ክብር በማጣት ወይም አክብሮት ባለመኖር መናገር።

ኃጥያቶችን ለማሰረየት መብት ይገባኛል ስላለ (ማቴ. ፱፥፪–፫ሉቃ. ፭፥፳–፳፩)፣ እራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ ብሎ ስለጠራ (ዮሐ. ፲፥፳፪–፴፮፲፱፥፯)፣ እና እርስን በሀይል ቀኝ ስቀመጥ እና በሰማይ ደመና ስመጣ ታዩኛላችሁ ስላላቸው (ማቴ. ፳፮፥፷፬–፷፭) አይሁዶች ኢየሱስ ስድብ ተናግሯል በማለት በብዙ ጊዜ ከሰውት ነበር። ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ባይሆን ኖሮ እነዚህ ክሶች እውነት ይሆኑ ነበር። በሳንሀድሪን ፊት ለፍርድ በቀረበበት ጊዜ በሀሰት ምስክሮች የተከሰሰበትም (ማቴ. ፳፮፥፶፱–፷፩) የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ተሳድቧል የሚል ነበር ስለክርስቶስ ፍጹም የሆነ እውቀትን ከመቀበል በኋላ በፍልጎት መካድ የሆነው መንፈስ ቅዱስን መስደብ ይቅርታ የሌለው ኃጢያት ነው (ማቴ. ፲፪፥፴፩–፴፪ማር. ፫፥፳፰–፳፱ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፯)።