በቀል ደግሞም ጠላትነት ተመልከቱ በጉዳት ወይም ለተከፉበት መበቀል። አምላካችሁ በበቀል ይመጣል, ኢሳ. ፴፭፥፬. በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ, ሮሜ ፲፪፥፲፱ (ሞር. ፫፥፲፭; ፰፥፳). የበቀል ጎራዴ በላያችሁ ላይ ያንዣብባል, ሞር. ፰፥፵–፵፩. በኃጢያተኞች ላይ በቀልን እወስዳለሁ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፲፯. አዳኝ በጥፋትና በበቀል ቀናት ይመጣል, ሙሴ ፯፥፵፭–፵፮.