የጥናት እርዳታዎች
ወደ ቄላስይስ መልእክት


ወደ ቄላስይስ መልእክት

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያለ መፅሐፍ። ይህ በመጀመሪያ ሐዋሪያው ጳውሎስ በኤጳፍራ ከተጎበኘ በኋላ ለቄላስይስ የጻፈው ደብዳቤ ነበር (ቄላ. ፩፥፯–፰)። ኤጳፍራ ጳውሎስን ቄላስይስ በከባድ ስህተት ውስጥ እየወደቁ እንዳሉ ነገረው—አንዳንድ የውጪ ስነስርዓቶችን በጥንቃቄ ስለሚከተሉ (ቄላ. ፪፥፲፮)፣ አንዳንድ ስጋዊ ፍላጎታቸውን ከእራሳቸው ስለሚያስወግዱ፣ እና መላእክትን ስለሚያመልኩ (ቄላ. ፪፥፲፰)እነርሱ ከሌሎች ሰዎች የተሻሉ ይመስላቸው ነበር። እንዚህ ድርጊቶች ቄላስይስን የተቀደሱ እንደሆኑ እንዲሰማቸው አደረጉአቸው። እነርሱም የሁለንታን ሚስጥሮች ከሌሎች የቤተክርስቲያን አባላት ይበልጥ እንደሚገባቸው ይሰማቸው ነበር። ቤዛነት የሚመጣው በክርስቶስ ብቻ እንደሆነ እነርሱን በማስተካከል እና እኛ ጥበበኛ መሆን እንደሚገባን እና እንድናገለግለው በደብዳቤው ውስጥ ጳውሎስ አስተማራቸው።

ምዕራፍ ፩ ጳውሎስ ለቄላስይስ የሰጠው ሰላምታ ነው። ምዕራፍ ፪–፫ ትምህርት የያዙ እናም ስለክርስቶስ ቤዛነት፣ ስለሀሰት አምልኮ አደጋ፣ እና ስለትንሳኤ አስፈላጊነት መግለጫዎችን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፬ ቅዱሳን በሁሉም ነገሮች ጠበበኛ መሆን እንዳለባቸው ያስተምራል።