የጥናት እርዳታዎች
ሌሂ፣ የኔፊ አባት


ሌሂ፣ የኔፊ አባት

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ቤተሰቡን እና ተከታዮቹን ከኢየሩሳሌም በምእራብ ክፍለ አለም ውስጥ ወደሚገኘው ወደ ቃል ኪዳን ምድር የመራ የእብራውያን ነቢይ። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ሌሂ በህዝቦቹ መካከል የነበረ የመጀመሪያ ነቢይ ነበር።

ሌሂ ከቤተሰቡ ጋር ከኢየሩሳሌም የሸሸው በጌታ ትእዛዝ መሰረት ነበር (፩ ኔፊ ፪፥፩–፬)። እርሱም በግብፅ ይተሸጠው ዮሴፍ ትውልድ ነበር (፩ ኔፊ ፭፥፲፬)። ጌታ ስለህይወት ዛፍ ራዕይ ሰጠው (፩ ኔፊ ፰፥፪–፴፭)። ሌሂና ወንድ ልጆቹ መርከብ ሰሩ እናም ወደ ምዕራብ ክፍለ አገር ተጓዙ (፩ ኔፊ ፲፯–፲፰)። እርሱና ትውልዶቹ በአዲሱ ምድር ተመሰረቱ (፩ ኔፊ ፲፰፥፳፫–፳፭)። ከመሞቱ በፊት፣ ሌሂ ልጆቹን ባረከ እናም ስለክርስቶስና በኋለኛው ቀናት መፅሐፈ ሞርሞን ስለመምጣቱ አስተማራቸው (፪ ኔፊ ፩፥፩–፬፥፲፪)።

መፅሐፈ ሌሂ

ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን ሲተረጉም በመፅሐፈ ሌሂ ነበር የጀመረው። ይህም ሞርሞን ከሌሂ ሰሌዳ አሳጥሮ የጻፈው መዝገብ ነበር። ከመፅሐፉ የተረጎማቸውን ፻፲፮ ገጾች ከነበረው በኋላ፣ ጆሴፍ፣ በመፅሀፈ ሞርሞን መተርጎም ጊዜ ለጆሴፍ እንደ ጸሀፊ ላገለገለው፣ ለማርቲን ሀርስ ያልታተመ መፅሐፍን ሰጠ። ገጾቹ ጠፉ። ጆሴፍ የጠፋውን ያልታተመ መፅሐፍ ለመተካት መፅሐፈ ሌሂን እንደገና አልተረጎመም፣ ነገር ግን በዚህ ምትክ ከዚህ ጋር የተገናኙ ታሪኮችን ከወርቅ ሰሌዳዎች ተረጎመ (ት. እና ቃ. ፫፲ መግቢያዎችን ተመልከቱ)። እነዚህ ታሪኮች አሁን የመፅሐፈ ሞርሞን የመጀመሪያው ስድስት መፅሐፎች ናቸው።