የጥናት እርዳታዎች
የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ


የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ

ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ።

በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደሚጠቀሙበት፣ የኅጢያት ዋጋን መክፈል ለኃጢያት ስራ ቅጣትን መቀበል፣ በዚህም ንስሀ ከሚገባው ኃጥያተኛ ላይ የኃጢያትን ውጤት ማስወገድ እና ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቅ መፍቀድ ማለት ነው። ለሰው ዘር ሁሉ ፍጹም የሆነ የኀጢያት ክፍያ ለማድረግ የሚችለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነበር። ይህን ለማድረግ የቻለው አለም ከመፈጠሯ በፊት በነበረው ታላቅ ሸንጎ በመመረጡ እና ቀድሞ በመሾሙ (ኤተር ፫፥፲፬ሙሴ ፬፥፩–፪አብር. ፫፥፳፯)፣ በመለኮታዊ ልጅነቱ፣ እና ኃጢያት በሌለው ህይወቱ ምክንያት ነው። የኀጢያት ክፍያው ለሰው ዘር ኀጥያቶች የተሰቃየበትን፣ የደሙ መፍሰስን፣ እና ሞቱን እና በተከተለው ከመቃብር በትንሳኤ መነሳቱን የሚጨምር ነው (ኢሳይያስ ፶፫፥፫–፲፪ሉቃ. ፳፪፥፵፬ሞዛያ ፫፥፭–፲፩አልማ ፯፥፲–፲፫ት. እና ቃ. ፲፱፥፲፮–፲፱)። በኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ ሁሉም ሰዎች ከማይሞቱ ሰውነቶች ጋር ከሞት ይነሳሉ (፩ ቆሮ. ፲፭፥፳፪)። የኃጢያት ክፍያም ከኀጥያታችን ምህረት የምናገኝበት እና ከእግዚአብሔር ለዘለአለም የምንኖርበት መንገዶች ሰጥቶናል። የአቅመ አዳም እድሜ ላይ የደረሰ እና ህግን የተቀበለ ሰው እነዚህን በረከቶች ለመቀበል የሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ካመነ፣ ለኀጥያቶቹ ንስሀ ከገባ፣ የደህናነትን ስርዓቶችን እና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ከተቀበለ ብቻ ነው። የአቅመ አዳም እድሜ ያልደረሱት እና ህግ የሌላቸው በኃጢያት ክፍያ በኩል ቤዛነት ያገኛሉ (ሞዛያ ፲፭፥፳፬–፳፭ሞሮኒ ፰፥፳፪)። ክርስቶስ ለኀጥያቶቻችን ክፍያ ካልሰጠ በስተቀር፣ ምንም ህግ፣ ስርዓት፣ ወይም መስዋዕት የፍትህን ጥያቄ ለመመለስ አይችልም፣ እና ሰው ወደ እግዚአብሔር ፊት ዳግሞ መመለስ አይችለም (፪ ኔፊ ፪) ብለው ቅዱስ መጻሕፍት በግልጽ አስተምረዋል።