የጥናት እርዳታዎች
ሕዝቅያስ


ሕዝቅያስ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የይሁዳ ህዝቦች ጻድቅ ንጉስ። ኢሳይያስ የይሁዳ ነቢይ በነበረበት ጊዜ፣ ለሀያ ዘጠኝ አመት ነገሰ (፪ ነገሥ. ፲፰–፳፪ ዜና ፳፱–፴፪ኢሳ. ፴፮–፴፱)። ኢሳይያስ ቤተክርስቲያኗን እና ሀገርን ለማስተካከል ረዳው። ጣዖት ማምለክ አስቆመ እናም የቤተመቅደስ አገልግሎቶችን በድጋሚ መሰረተ። የሕዝቅያስ ህይወት በጸሎት እና እምነት ምክንያት ለአስራ አምስት አመት ተራዘመ (፪ ነገሥ. ፳፥፩–፯)። የንግሰ ዘመኑ የመጀመሪያ ክፍል ሀብታም ነበር፣ ነገር ግን በሶሪያ ንጉስ ላይ ማመጹ (፪ ነገሥ. ፲፰፥፯) ለሁለት ጊዜ በሶሪያ እንዲወረር አደረገው፥ የመጀመሪያው በኢሳይያስ ፲፥፳፬–፴፪ ውስጥ፣ ሁለተኛውም በ፪ ነገስት ፲፰፥፲፫–፲፱፥፯ ውስጥ ተገልጸዋል። ለሁለተኛ ጊዜ በተወረረበት፣ ኢየሩሳሌም በጌታ መልዓክ ዳነች (፪ ነገሥ. ፲፱፥፴፭)።