የጥናት እርዳታዎች
ኢኖስ፣ የያዕቆብ ልጅ


ኢኖስ፣ የያዕቆብ ልጅ

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የጸለየና በክርስቶስ እምነቱ በኩል ለኃጢያቶቹ ስርየትን ያገኘ የኔፋውያን ነቢይና መዝገብ ጠባቂ (ኢኖስ ፩፥፩–፰)። ጌታ ከኢኖስ ጋር መፅሀፈ ሞርሞንን ለናማናውያን ለማምጣት ቃል ኪዳን ገባ (ኢኖስ ፩፥፲፭–፲፯)።

መፅሐፈ ኢኖስ

ኢኖስ ወደ ጌታ ለግል ምህረት፣ ለህዝቦቹና፣ ለሌሎችስለጸለየበት የሚነግር በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኝ መፅሐፍ። ጌታ መፅሐፈ ሞርሞን እንደሚጠበቅ እና በወደፊት ቀን ላማናውያን እንዲያገኙት እንደሚደረግ ጌታ ቃል ገባለት። ምንም እንኳን መፅሐፉ አንድ ምዕራፍ ብቻ ያለው ቢሆንም፣ አምላኩን በጸሎት ስለፈለገ፣ በእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥ በመሆን ስለኖረ፣ እናም ከመሞቱ በፊት በቤዛው እውቀት ስለተደሰተ ሰው ሀይለኛ ታሪክ መዝግቧል።