የጥናት እርዳታዎች
ማርቆስ


ማርቆስ

የማርያም ልጅ ነበር (የሐዋ. ፲፪፥፲፪)፤ ደግሞም የበርናባስ ዘመድ ሳይሆን አይቀርም (ቄላ. ፬፥፲)። ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር በመጀመሪያው ጉዞአቸው ከኢየሩሳሌም ሄደ እናም በጴርጌም ከእነርሱ ተለየ (የሐዋ. ፲፪፥፳፭፲፫፥፭፣ ፲፫)። በኋላም ከበርናባስ ጋር ወደ ቆጵሮስ ሄደ (የሐዋ. ፲፭፥፴፯–፴፱)። በሮሜ ውስጥ ከጳውሎስ ጋር ነበር (ቄላ. ፬፥፲ፊልሞ. ፩፥፳፬)፣ እናም ከጴጥሮስ ጋር በባቢሎን (ምናልባት በሮሜም) ውስጥ ነበር (፩ ጴጥ. ፭፥፲፫)። በመጨረሻም ከጢሞቴዎስ ጋር በኤፌሶን ነበር (፪ ጢሞ. ፬፥፲፩)።

የማርቆስ ወንጌል

የአዲስ ኪዳን ሁለተኛ መፅሐፍ። የማርቆስ ወንጌል ምናልባት የተጻፈው በጴጥሮስ አመራር ስር ነበር። አላማው ጌታን በሰዎች መካከል እንደኖረና እንደሰራ የእግዚአብሔር ልጅ ለመግለፅ ነበር። ማርቆስ፣ በሀይል እና በትሁትነት፣ ሌሎች ኢየሱስን እንዴት እንደተመለከቱት ገለጸ። ባህል እንደሚገልጸው ከጴጥሮስ ሞት በኋላ፣ ማርቆስ ግብፅን ጎበኝ፣ የእስክንድርያን ቤተክርስቲያን አደራጀ፣ እናም በሰማዕትነት ሞተ።

በማርቆስ ወንጌል ውስጥ የተገለጹትን የአዳኝ ህይወት ድርጊቶችዝርዝር፣ የወንጌሎች ስምምነትን ተመልከቱ።