የጥናት እርዳታዎች
ዜና ማዋእል


ዜና ማዋእል

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ ሁለት መጻህፍቶች። እነዚህም ከፍጥረት ጀምሮ አይሁድ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ እስከታወጀበት ድረስ የነበሩትን ድርጊቶች አጭር ታሪክ ይዘረዝራሉ።

ዜና ማዋእል ቀዳማዊ

ምዕራፍ ፩–፱ ከአዳም እስከ ሳኦል የነበሩትን ትውልዶች ይዘረዝራሉ። ምዕራፍ ፲ የሳኦል ሞትን ይዘረዝራል። ምዕራፍ ፲፩–፳፪ የዳዊት ግዛት ጋር የተያያዙትን ድርጊቶች ይገልጻል። ምዕራፍ ፳፫–፳፯ ሰለሞን እንደነገሰና ሌዋውያን በስነስርዓት እንደተደራጁ ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፳፰ ዳዊት ሰለሞንን ቤተመቅደስ እንዲገነባ እንዳዘዘው ይገልጻል። ምዕራፍ ፳፱ የዳዊት ሞትን ይመዘግባል።

ዜና ማዋእል ካልዕ

ምዕራፍ ፩–፱ ከሰለሞን ግዛት ጋር የተያያዙትን ድርጊቶች ይገልጻል። ምዕራፍ ፲–፲፪ አንድ የነበረው የእስራኤል መንግስት ወደ ሰሜንና ደቡብ ግዛት ስለተከፋፈለበት ስለሰለሞን ልጅ ሮብዓም ግዛት ይናገራሉ። ምዕራፍ ፲፫–፴፮ ናቡከደነዖር የአይሁድን መንግስት በምርኮ እስከሚይዝበት ድረስ የነበሩትን የተለያዩ ንጎሶች ይገልጻል። መፅሐፉም ቂሮስ በምርኮ የተያዙት የአይሁድ ልጆች ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ በሚያውጅበት ይፈጸማል።