የጥናት እርዳታዎች
ንፍታሌም


ንፍታሌም

ከያዕቆብ አስራ ሁለት ልጆች ስድስተኛው እና የራሄል ገረድ ባላ ሁለተኛ ልጅ ነበር (ዘፍጥ. ፴፥፯–፰)። ንፍታሌም አራት ወንድ ልጆች ነበሩት (፩ ዜና ፯፥፲፫)።

የንፍታሌም ጎሳዎች

ያዕቆብ ለንፍታሌም የሰጠው በረከቶች በኦሪት ዘፍጥረት ፵፱፥፳፩ ውስጥ ተመዝግበዋል። ሙሴ ለጎሳው የሰጠው በረከት በኦሪት ዘዳግም ፴፫፥፳፫ ውስጥ ተመዝግቧል።