የጥናት እርዳታዎች
ዳንኤል


ዳንኤል

በብሉይ ኪዳን በትንቢተ ዳንኤል ውስጥ ዋናው ሰው። የእግዚአብሔር ነቢይና የታላቅ እምነት ሰው።

ስለወላጆቹ ምንም አይታወቅም፣ ነገር ግን የንጉሶች ትውልድ የሆነ ይመስላል (ዳን. ፩፥፫)። ወደ ባቢሎን በምርኮ ተወስዶ ነበር፣ በዚያም የብልጣሶር ስም ተሰጠው (ዳን. ፩፥፮–፯)። ዳንኤል እና ሌሎች ሶስት ምርኮኛዎች የንጉሱን ምግብ በጽድቅ ምክንያት አንበላም አሉ (ዳን. ፩፥፰–፲፮)።

ዳንኤል ህልሞችን ለመተርጎም በነበረው ሀይል ምክንያት በናቡከደነዖር እና በዳርዮስ ተወዳጅ ሆነ (ዳን. ፪)። በግድግዳ ላይ የነበረውን የእጅ ጽሁፍንም አንብቦ ተረጎመ (ዳን. ፭)። ጠላቶቹ በእርሱ ላይ አሴሩበት፣ እና ወደ አምበሶች ጉድጓድ ተጣለ፣ ነገር ግን ጌታ ህይወቱን አዳነ (ዳን. ፮)።

ትንቢተ ዳንኤል

መፅሐፉ ሁለት ክፍሎች አሉት፥ ምዕራፍ ፩–፮ ስለዳንኤልና ስለሶስቱ ጓደኞቹ ታሪክ ናቸው፤ ምዕራፍ ፯–፲፪ ዳንኤል ያያቸው ነቢያዊ ራዕዮች ናቸው። መፅሐፉ ለእግዚአብሔር እውነተኛ የመሆንን አስፈላጊነት ያስተምራል እናም ጌታ ታማኝን እንደሚባርክ በምሳሌ ያሳያል።

መፅሐፉ ከሰጣቸው ታላቁ የንጉስ ናቡከደነዖር ህልም ትርጉም ነው። በህልሙ ውስጥ የእግዚአብሔር መንግስት በመጨረሻው ቀናት ከተራራው እንደ ተፈነቀለ ድንጋይ ጋር ይመሳሰላል። ድንጋዩም ምድርን በሙሉ እስከሚሸፍን ድረስ ይንከባለላል (ዳን. ፪፤ ደግሞም ት. እና ቃ. ፷፭፥፪ ተመልከቱ)።