የጥናት እርዳታዎች
ጸጋ


ጸጋ

ወንዶች እና ሴቶች ታማኝ ከሆኑ፣ ንስሀ ከገቡና፣ እና ትእዛዛትን ለማክበር ጥረታቸውን ሁሉ በማድረግ በዚህ ህይወት በረከቶችን እና ዘለአለማዊ ህይወትን እና ዘለአለማዊነትን ለማግኘት ከእግዚአብሔር የሚመጣ የሚያስችል ሀይል። እንደዚህ አይነት እርዳታ ወይም ጥንካሬ የሚሰጠው በእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር በኩል ነው። እያንዳንዱ ስጋዊ ሰው በአዳም ውድቀት ምክንያት እና በሰው ደካማነት ምክንያት መለኮታዊ ጸጋ ያስፈልገዋል።