የጥናት እርዳታዎች
ጴጥሮስ


ጴጥሮስ

በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ በቅፍርናሆም ከሚስቱ ጋር ይኖር የነበረ የቤተሳይዳ አሳ አጥማጅ ጴጥሮስ በመጀመሪያ ስምዖን (፪ ጴጥ. ፩፥፩) ተብሎ ይታወቅ ነበር። ኢየሱስ የጴጥሮስን ባለቤት እናትን ፈወሰ (ማር. ፩፥፳፱–፴፩)። ጴጥሮስ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር የኢየሱስ ክርስቶስ ድቀ መዛሙርት እንዲሆን ተጠርቶ ነበር (ማቴ. ፬፥፲፰–፳፪ማር. ፩፥፲፮–፲፰ሉቃ. ፭፥፩–፲፩)። “ገላጭ” ወይም “አለት” የሚል ትርጉም ያለው ኬፋ የሚባለው ስሙ ለእርሱ በጌታ የተሰጠው ነበር (ዮሐ. ፩፥፵–፵፪ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐ. ፩፥፵፪ [ተጨማሪ])። አዲስ ኪዳን የጴጥሮስን አንዳንድ ስጋዊ ደካማነቶችን ቢጠቅስም፣ ይህም እነዚህን እንዳሸነፈና በኢየሱስ ክርስቶስ በነበረው እምነት ጠንካራ እንደሆነ ያሳያሉ።

ጴጥሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መሰከረ (ዮሐ. ፮፥፷፰–፷፱)፣ እናም ጌታ የመንግስትን ቁልፎች በምድር ላይ እንዲይዝ መረጠው (ማቴ. ፲፮፥፲፫–፲፱)። በመቀየሪያ ተራራ ላይ፣ ጴጥሮስ የተቀየረውን አዳኝ፣ እናም ሙሴንና ኢልያ (ኤልያስን) አየ (ማቴ. ፲፯፥፩–፱)።

ጴጥሮስ በጊዜው ዋና ሐዋሪያ ነበር። ከአዳኝ ሞት፣ ትንሳኤ፣ እና ማረግ በኋላ፣ ቤተክርስቲያኗን ሰበሰበ እና የአስቆሮቱ ይሁዳን ለመተካት ሐዋሪያ እንዲመረጥ መመሪያ ሰጠ (የሐዋ. ፩፥፲፭–፳፮)። ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ ሽባ የነበረ ሰውን ፈወሱ (የሐዋ. ፫፥፩–፲፮) እናም ከእስር ቤት በተአምራት ተለቀቁ (የሐዋ. ፭፥፲፩–፳፱፲፪፥፩–፲፱)። በጴጥሮስ አገልግሎት ነው ወንጌሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአህዛቦች የተከፈተው (የሐዋ. ፲–፲፩)። በኋለኛው ቀናት፣ ጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር፣ ከሰማይ መጡ እና የመልከ ጼዴቅ ክህነትን እና የዚህን ቁልፎች ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውደሪ ሰጡ (ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፪–፲፫፻፳፰፥፳)።

መጀመሪያይቱ የጴጥሮስ መልእክት

የመጀመሪያው መልእክት ከባቢሎን (ምናልባት ሮሜ) የተጻፈ ነበር እናም አሁን እስያ ታናሽ ተብሎ ለሚታወቀው ቦታ ኒሮ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ከጀመረ ከቅርብ ጊዜ በኋላ ነበር የተላከው።

ምዕራፍ ፩ ስለክርስቶስ እንደ ቤዛ አስቀድሞ መቀባት ይናገራል። ምዕራፍ ፪–፫ ክርስቶስ የቤተክርስቲያኗ ዋና የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነ፣ ቅዱሳን ልዑል ክህነትን እንደያዙ፣ እና ክርስቶስ በነፍስ እስር ቤት ውስጥ እንደሰበከ ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፬–፭ ወንጌሉ ለምን ለሙታን እንደሚሰበክ እና ለምን ሽማግሌዎች መንጋዎችን መመገብ እንዳለባቸው ይገልጻሉ።

ሁለተኛይቱ የጴጥሮስ መልእክት

ምዕራፍ ፩ ቅዱሳንን ጥሪአቸውን እና ምርጫቸውን እንዲያረጋግጡ ይለምናል። ምዕራፍ ፪ ስለሀሰት አስተማሪዎች ያስጠነቅቃል። ምዕራፍ ፫ ስለኋለኛው ቀናት እና ስለክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ይናገራል።