የጥናት እርዳታዎች
ያዕቆብ፣ የሌሂ ልጅ


ያዕቆብ፣ የሌሂ ልጅ

የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ እና በ፪ ኔፊ እና በያዕቆብ መፅሀፎች ውስጥ የተለያዩ ስብከቶች ጸሀፊ (፪ ኔፊ ፮–፲፩ያዕቆ. ፩–፯)።

መፅሐፈ ያዕቆብ

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ሶስተኛ መፅሐፍ። ምዕራፍ ፩ ኔፊ የተቀደሱ መዝገቦች ለያዕቆብ አሳልፎ እንደሰጠ እና ከእዚያም ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሴፍን ለህዝቡ ካህናት እና መምህሮች እንዲሆኑ ቀደሰ። ምዕራፍ ፪–፬ ህዝቡን በስነምግባር ንጹህ እንዲሆኑ የሚገስጹ ስብከቶች። ያዕቆብ ደግሞም ስለሚያድነው መሲህ መምጣት አስተማረ፣ እና በሚመጣበት ጊዜ በእስራኤል ውስጥ ለምን አንዳንዶች እንደማይቀበሉት ምክንያትን ሰጠ። ምዕራፍ ፭–፮ የያዕቆብን ምስክር እና ስለእስራኤል ህዝብ ታሪክ እና ተልዕኮ ነቢያዊ ምሳሌ የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፯ በያዕቆብ መለኮታዊ ምስክር ስለተሸነፈው ሼረም ስለሚባለው የተማረ ተቃዋሚ ታሪክ ይዟል።