የጥናት እርዳታዎች
ላማናውያን


ላማናውያን

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያሉ ህዝቦች፣ ብዙዎቹ የሌሂ የመጀመሪያ ልጅ የላማን ትውልዶች ነበሩ። በኔፊ እና በትውልዶቹ የማይገባ ነገሮች እንደተደረጉባቸው ይሰማቸው ነበር (ሞዛያ ፲፥፲፩–፲፯)። በዚህም ምክንያት፣ በኔፋውያን ላይ አመጹ እናም ብዙም ጊዜ የወንጌል ትምህርቶችን አስወገዱ። ነገር ግን፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ከትንሽ ጊዜ በፊት፣ ላማናውያን ወንጌልን ተቀበሉ እናም ከኔፋውያን ይልቅ ጻድቅ ነበሩ (ሔለ. ፮፥፴፬–፴፮)። ክርስቶስ አሜሪካን ከጎበኘ ከሁለት መቶ አመት በኋላ፣ ላማናውያን እና ኔፋውያን ክፉዎች ሆኑ እናም እርስ በራስ መዋጋት ጀመሩ። በ፬፻ ዓ.ም. አካባቢ፣ ላማናውያን የኔፋውያን ህዝቦችን በሙሉ አጠፉ።