የጥናት እርዳታዎች
ሎጥ


ሎጥ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የሐራን ልጅ እና የአብርሐም የወንድም ልጅ (ዘፍጥ. ፲፩፥፳፯፣ ፴፩አብር. ፪፥፬)። ሐራን በዑር ውስጥ በርሀብ ምክንያት ሞተ (አብር. ፪፥፩)። ሎጥ ከዑር ከአብርሐም እና ከሳራ ጋር ወጣ እናም ከእነርሱ ጋር ወደከነዓን ተጓዘ (ዘፍጥ. ፲፪፥፬–፭)። ሎጥ በሰዶም ለመኖር መረጠ። በህዝቡ ክፉነት ምክንያት ጌታ ሰዶምን ከማጥፋቱ በፊት ሎጥ እንዲሸሽ እንዲያስጠነቅቁት ጌታ መልእክተኞች ላከ (ዘፍጥ. ፲፫፥፰–፲፫፲፱፥፩፣ ፲፫፣ ፲፭)፤ ነገር ግን፣ የሎጥ ባለቤት ድምሰሳውን ለመመልከት ወደኋላ ተመለከተች እናም የጨው ሐውልት ሆነች (ዘፍጥ. ፲፱፥፳፮)። አዲስ ኪዳን ስለሎጥ ይጠቅሳሉ (ሉቃ. ፲፯፥፳፱፪ ጴጥ. ፪፥፮–፯)። ከአብርሐም ከተለያየ በኋላ ስለነበረው ህይወቱ በዘፍጥረት ፲፫፲፬፣ እና ፲፱ ተገልጸዋል።