የጥናት እርዳታዎች
መጋቢ፣ መጋቢነት


መጋቢ፣ መጋቢነት

የሌላን ጉዳይ ወይም ንብረት የሚያስተዳድር ሰው። መጋቢ የሚያስተዳድረው መጋቢነት ይባላል። በምድር ያሉት ነገሮች ሁሉ የጌታ ናቸ፤ እኛም የእርሱ መጋቢዎች ነን። ለጌታ ሀላፊዎች ነን፣ ነገር ግን በመጋቢነታችን በእግዚአብሔር ስልጣን ለተሰጣቸው ወኪሉ ሀተታ ለመስጠት እንችላለን። ከጌታ ወይም ስልጣን ካላቸው አገልጋዮቹ የአገልግሎት ጥሪ ስንቀበል፣ ያም መጋቢነት በመንፈሳዊ እና በምድራዊ ጉዳዮች ላይ ለመሆን ይችላል (ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፬)።