የጥናት እርዳታዎች
ሆሳዕና


ሆሳዕና

“እባክህ አድነን” የሚል ትርጉም ያለው እና በሙገሳና በአምልኮት የሚጠቀሙበት የዕብራውያን ቃል።

ጌታ እስራኤልን ወደ ቃል ኪዳን ምድር ያዳነበትን በሚያከብሩበት የዳስ በዓል፣ ሰዎች የመዝሙር ፻፲፰ ቃላትን እየደጋገሙ ይላሉ እናም ዘንባባን ያውለበልባሉ። ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በድል በገባበት ጊዜ፣ ህዝቦቹ “ሆሳዕና” በማለት ጮሁ እናም ኢየሱስ እየጋለበ እንዲሄድበት ዘንባባ ቅርንጫፎችን አነጠፉ፣ በዚህም ኢየሱስ እስራኤልን በጥንት ያዳነ አንድ ጌታ እንደሆነ እንደገባቸው አሳዩ (መዝ. ፻፲፰፥፳፭–፳፮ማቴ. ፳፩፥፱፣ ፲፭ማር. ፲፩፥፱–፲ዮሐ. ፲፪፥፲፫)። እነዚህ ህዝቦች ክርስቶስን ለረጅም ጊዜ ይጠበቅበት እንደነበረው መሲሕ አወቁት። ሆሳዕና የሚባለው ቃል በሁሉም ዘመናት መሲሕ የሚከበርበት ሆኗል (፩ ኔፊ ፲፩፥፮፫ ኔፊ ፲፩፥፲፬–፲፯)። የሆሳዕና ጩኸት በከርትላንድ ቤተመቅደስ በሚቀደስ ጊዜም ተጨምሯል (ት. እና ቃ. ፻፱፥፸፱) እና አሁንም የእዚህ ዘመን ቤተመቅደሶች የመቀደስ ክፍል ነው።