የጥናት እርዳታዎች
አስቴር


አስቴር

ታላቅ እምነት የነበራት እና በመፅሐፈ አስቴር ውስጥ ዋና ባለታሪክ።

መፅሐፈ አስቴር

ህዝቦቿን ከጥፋት ለማዳን ንግስት አስቴር የነበራት ታላቅ ብርቱነትን የሚያሳይ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኝ መፅሐፍ።

ምዕራፍ ፩–፪ የአይሁዳ ሴትና መርዶክዮስ የሚባለው የአይሁዳ ሰው በጉዲፈቻ ያሳድጋት የነበረችው ሴት ልጅ በውበቷ ምክንያት የፋርስ ንግስት እንድትሆን እንዴት እንደተመረጠች ይነግራሉ። ምዕራፍ ፫ በንጉሱ ቤት ዋና አለቃ የነበረው ሀማን መርዶክዮስን እንደጠላና የአይሁዳ ህዝቦችን በሙሉ ለመግደል አዋጅ እንዳገኘ ይገልጻል። ምዕራፍ ፬–፲ አስቴር፣ እራሷን በአደጋ ላይ በመጣል፣ ዜግነቷን ለንጉሱ እንዴት እንደገለጸችና የአዋጁን ለውጥ እንዳመጣች ይናገራሉ።