ስለሁሉም የሰው ዘር፣ ወንድ እና ሴቶች፣ የሚናገር ነው። ሁሉም ወንዶችና ሴቶች የሰማይ አባት የመንፈስ ልጆች ናቸው። በሚሞት ሰውነት ሲወለዱ፣ ስጋዊና ሟች ሰውነቶችን ተቀበሉ። እነዚህ ሰውነቶች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር መልክ ነበር (ዘፍጥ. ፩፥፳፮–፳፯)። አስፈላጊ የሆኑትን ስነስርዓቶች ለመቀበል ብቁ የሆኑ ወንዶች እና ሴቶች፣ ቃል ኪዳኖችን በማክበር፣ እናም የእግዚአብሔር ትእዛዛትን በማክበር ወደዘለአለማዊነታቸው ለመግባትና እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ይችላሉ።
የሰው እንደ እግዚአብሔር አይነት ለመሆን ያለው ችሎታ