የጥናት እርዳታዎች
ሞርሞን፣ የኔፋውያን ነቢይ


ሞርሞን፣ የኔፋውያን ነቢይ

የኔፋውያን ህዝብ ነቢይ፣ የወታደሮች ጄነራል፣ እና የመፅሐፈ ሞርሞን መዝገብ ጠባቂ። ሞርሞን በ፫፻፲፩–፫፻፹፭ ም.ዓ. አካባቢ ይኖር ነበር (ሞር. ፩፥፪፣ ፮፮፥፭–፮፰፥፪–፫)። ከአስራ አምስት አመቱ ጀምሮ በብዙ ህይወቱ የወታደሮች መሪ ነበር (ሞር. ፪፥፩–፪፫፥፰–፲፪፭፥፩፰፥፪–፫)። አማሮን ሞሮኒን በመዝገቦቹ ሀላፊነት ለመውሰድና መዝገቦችን ለመጠበቅ እንዲዘጋጅ መመሪያ ሰጠው (ሞር. ፩፥፪–፭፪፥፲፯–፲፰)። የህይወቱን ታሪክ ከመዘገበ በኋላ፣ ሞርሞን የኔፊን ታላቅ ሰሌዳ በሞርሞን ሰሌዳዎች ላይ በማሳጠር ጻፈ። በኋላም ይህን ቅዱስ መዝገብ ለልጁ ለሞሮኒ አሳልፎ ሰጠ። እነዚህ ሰሌዳዎች ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን የተረጎመባቸው ሰሌዳዎች ክፍል ነበሩ።

የሞርሞን ቃላት

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ትንሹ መፅሐፍ። በመፅሐፈ ኦምኒ ውስጥ አማሌቅ የመጨረሻ ቃላት እና በመፅሐፈ ሞሳያ የመጀመሪያ ቃላት መካከል፣ የመዝገቦቹ በሙሉ አዘጋጁ ሞርሞን ይህን ትንሽ ተጨማሪ ጻፈ። (“ስለመፅሐፈ ሞርሞን አጭር መግለጫ” በመፅሐፈ ሞርሞን መጀመሪያ ውስጥ ተመልከቱ።)

መፅሐፈ ሞርሞን

መፅሐፈ ሞርሞን ተብሎ በሚታወቀው ቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ የሚገኝ የተለየ መጽሐፍ። ምዕራፍ ፩–፪ የኔፋውያን ነቢይ አማሮን ሞርሞን ሰሌዳዎችን መቼና የት እንደሚያገኛቸው ስላስተማረው ይናገራሉ። ደግሞም፣ ታላቁ ጦርነት ተጀመረ፣ እናም ሶስቱ ኔፋውያን በህዝብ ክፋት ምክንያት ተወሰዱ። ምዕራፍ ፫–፬ ሞርሞን ለህዝቦቹ ንስህ ስለመግባት መስበኩ ይናገራሉ። ነገር ግን ስሜት የሚሰማቸው አልነበሩም እናም በእስራኤል ውስጥ ከነበረው ክፋት ሁሉ በላይ ታላቅ ክፋት ተባዛ። ምዕራፍ ፭–፮ በኔፋውያን እና በላማናውያን መካከል የመጨረሻ ጦርነት ይመዘግባሉ። ሞርሞን ከብዙዎቹ የኔፋውያን ህዝቦች ጋር ተገደለ። በምዕራፍ ፯ ውስጥ፣ ከመሞቱ በፊት፣ ሞርሞን እዚያ ያሉትን እና የወደፊት ህዝቦቹን ንስሀ እንዲገቡ ጠራ። ምዕራፍ ፰–፱ በመጨረሻም የሞርሞን ልጅ ሞሮኒ ብቻ በህይወት እንደቀረ ይመዘግባል። የኔፋውያን ህዝብ መጨረሻን የሚጨምር የመጨረሻውን የሞትና የጭፍጨፋ ትእይንትን መዘገበ፣ እናም ለወደፊት ትውልዶችና ይህም መዝገብ ለሚያነቡት መልእክት ጻፈ።