የጥናት እርዳታዎች
የከርትላንድ ቤተመቅደስ፣ ኦሀዮ (ዮ.ኤስ.ኤ.)


የከርትላንድ ቤተመቅደስ፣ ኦሀዮ (ዮ.ኤስ.ኤ.)

በዚህ ዘመን በቤተክርስቲያኗ የተገነባ የመጀመሪያ ቤተመቅደስ። ቅዱሳን በከርትላንድ ውስጥ፣ በጌታ ትእዛዝ መሰረት ገነቡት (ት. እና ቃ. ፺፬፥፫–፱)። የቦታው አንድ አላማም ብቁ የሆኑ የቤተክርስቲያኗ አባላት መንፈሳዊ ሀይል፣ ስልጣን፣ እና መብራራትን ለመቀበል እንዲችሉ ነበር (ት. እና ቃ. ፻፱–፻፲)። በመጋቢት ፳፯፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) ተመረቀ፤ የመመረቂያው ጸሎት የተሰጠውም በራዕይ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ነበር (ት. እና ቃ. ፻፱)። በእዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ ጌታ ብዙ አስፈላጊ ራዕዮችን ሰጠ እናም አስፈላጊ የሆኑትን የክህነት ቁልፎችንም ዳግሞ መለሰ (ት. እና ቃ. ፻፲፻፴፯)። በዛሬ ቤተመቅደሶች ውስጥ የሚሰጡትን ሙሉ የመንፈስ ስጦታዎችን ለመስጠት አልተጠቀሙበትም ነበር።