የጥናት እርዳታዎች
ኦሪት ዘኁልቁ


ኦሪት ዘኁልቁ

የብሉይ ኪዳን አራተኛ መፅሐፍ። ሙሴ ኦሪት ዘኁልቁን ጽፏል። ኦሪት ዘኁልቁ ከሲና ተራራ እስከ ከነዓን ድንበር በሞአብ ሜዳዎች የእስራኤልን ጉዞ ታሪክ ይነግራል። የሚያስተምረው አንዱ አስፈላጊ ትምህርት ቢኖር የእግዚአብሔር ህዝብ በውጤታማነት ለመቀጠል በእምነት፣ የእርሱን ቃል ኪዳን በማመን መሄድ እንዳለባቸው ነው። ትእዛዝን ባለማክበር እግዚአብሔር እስራኤልን ስለቀጣበት ይናገራል እናም ስለእስራኤል ህግጋት መረጃዎች ይሰጣል። የመፅሐፉ ስም የመጣው በአጠቃላይ የህዝቡ ቆጠራ ላይ በነበሩት የህዝቡ ቁጥሮች ነው (ዘኁል. ፩–፪፳፮)።

ምዕራፍ ፩–፲ ስለእስራኤላውያን ከሲና ለመሄድ ዝግጅት ይናገራሉ። ምዕራፍ ፲፩–፲፬ ጉዞውን፣ ወደ ከነዓን ሰላዮችን ስለመላክ፣ እና እስራኤል ወደ ቃል ኪዳን ምድር ለመግባት እምቢ ስለማለታቸው ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፲፭–፲፱ የተለያዩ ህግጋትን እና የታሪክ ድርጊቶችን ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፳–፴፮ ህዝቡ በምድረበዳ ያሳለፉበት የመጨረሻ አመት ታሪክ ናቸው።