የጥበብ ቃል ለቅዱሳን ስጋዊ እና መንፈሳዊ ጥቅም ጌታ የገለጸው የጤንነት ህግ (ት. እና ቃ. ፹፱)። አሁን ይህም የጥበብ ቃል ተብሎ ይታወቃል። ጌታ ሁልጊዜም ተከታዮቹን የጤና መሰረታዊ መርሆችን ያስተምራል። ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ የትኛውን ምግብ መመገብ እንደሚገባ እና የትኛውን ምግብ ማስወገድ እንደሚገባ፣ እንዲሁም የጥበብ ቃልን ለሚያከብሩ ምድራዊ እና መንፈሳዊ በረከቶች ቃል ኪዳን በመግባት ገለጸ። የወይን ጠጅና የሚያሰክርን ነገር ሁሉ አትጠጡ, ዘሌዋ. ፲፥፱. የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፥ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል, ምሳ. ፳፥፩. የሚያሰክርም መጠጥ ለሚጠጡት መራራ ይሆናል, ኢሳ. ፳፬፥፱. ዳንኤልም በንጉሡ መብልና በሚጠጣው ጠጅ እራሱን አላረከሰም, ዳን. ፩፥፰. ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል, ፩ ቆሮ. ፫፥፲፮–፲፯. ሰካሮች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም, ፩ ቆሮ. ፮፥፲ (ገላ. ፭፥፳፩). ከስጋ እንዲቆጠብ የሚከለክልም በእግዚአብሔር የተሾመ አይደለም, ት. እና ቃ. ፵፱፥፲፰–፳፩. ከምድር የሚመጡት ነገሮች ሁሉ በብልጫ ሳይሆን በጥበብ ይጠቀሙባቸው, ት. እና ቃ. ፶፱፥፳. ጌታ የወይን ጠጅ፣ የሚያሰክር መጠጥ፣ ትምባሆ፣ እና ትኩስ መጠጦችን እንዳይጠቀሙባቸው ቅዱሳንን መከረ, ት. እና ቃ. ፹፱፥፩–፱. ለምለሞች፣ ፍሬዎች፣ ስጋ፣ እና እህል ለሰው እና ለእንስሳት ጥቅም ተመድበዋል, ት. እና ቃ. ፹፱፥፲–፲፯. ለጥበብ ቃል ታዛዥ መሆን ምድራዊ እና መንፈሳዊ በረከቶችን ያመጣል, ት. እና ቃ. ፹፱፥፲፰–፳፩.