የጥናት እርዳታዎች
ይቅርታ ማድረግ


ይቅርታ ማድረግ

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እንደሚጠቀሙበት፣ ይቅርታ ማድረግ ከሁለቱ ነገሮች አንዱ ነው፥ (፩) እግዚአብሔር ሰዎችን ይቅርታ ሲያደርግ፣ ለኃጢያት የተመደበውን ቅጣት ይሰርዛል ወይም ያስወግዳል። በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል፣ በመግደል ወይም በመንፈስ ቅዱስ ላይ ይቅርታ የሌለውን ኃጢያት ከፈጸሙት በስተቀር፣ የኃጢያቶች ስርየት ንስሀ ለሚገቡት በሙሉ ይገኛል። (፪) ሰዎች ለእርስ በራስ ይቅርታ ሲሰጣጡ፣ እርስ በራስ በክርስቶስ አይነት ፍቅር ይዋደዳሉ እናም ላስከፉዋቸውም ምንም መጥፎ ስሜት አይኖራቸውም (ማቴ. ፭፥፵፫–፵፭፮፥፲፪–፲፭ሉቃ. ፲፯፥፫–፬፩ ኔፊ ፯፥፲፱–፳፩)።