የጥናት እርዳታዎች
ናቩ፣ ኢለኖይ (ዮ.ኤስ.ኤ.)


ናቩ፣ ኢለኖይ (ዮ.ኤስ.ኤ.)

በ፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) በኢለኖይ ግዛት ውስጥ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የተመሰረተ ከተማ። የሚገኘው ከሴንት ሉውስ ከተማ ፪፻ ማይል (፫፻፳ ኪሎ ሜትር) ከወንዙ በላይ በምስስፒ ወንዝ አጠገብ ነው።

በምዙሪ ግዛት በተሰደዱበት ምክንያት፣ ቅዱሳን ወደ ፪፻ ማይል (፫፻፳ ኪሎ ሜትር) ወደ ሰሜን ምስራቅ አካባቢ፣ የምስስፒ ወንዝን በመሻገር፣ ጥሩ ሁኔታዎችን ወደሚያገኙበት ወደ ኢለኖይ ሄዱ። ከጊዜ በኋላም፣ ቅዱሳን ገና ባልለመለመ ኮሜርስ ከተማ አጠገብ ምድር ገዙ። ከአንዳንድ ህንጻዎች በስተቀር፣ ይህ ምድር አረንቋማ ነበር ቅዱሳን ከምድሩ ውሀውን አደረቁ እና ቤቶቻቸውን መሰረቱ። ጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰቡን በእንጨት በተሰራ ትንሽ ቤት ውስጥ አስገባ። ኮሜርስ የሚባለው የከተማው ስም ወደ ናቩ ተቀየረ፣ ይህም ከዕብራውያን “ወብታማ” ከሚባለው ቃል ነው።

የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ብዙ ክፍሎች የተመዘገቡት በናቩ ውስጥ ነው (ት. እና ቃ. ፻፳፬–፻፳፱፻፴፪፻፴፭)። ቅዱሳን በናቩ ቤተመቅደስ እንዲገነቡ ተነገራቸው (ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፳፮–፳፯)። ከቤቶቻቸው በ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) ተነድተው ከመሰደዳቸው በፊት ቤተመቅደስን ሰሩ እናም የፅዮን ካስማዎችን አደራጁ። በመሳደዳቸው ምክንያት፣ ቅዱሳን ከእዚያ ቦታ ወጡና ወደ ምዕራብ ተጓዙ።