አህዛቦች በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደሚጠቀሙበት፣ አህዛብ የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። አንዳንድ ጊዜ ይህም የእስራኤል ዘር ያልሆኑ ህዝቦችን፣ አንዳንድ ጊዜ የአይሁዳ ዘር ያልሆኑ ህዝቦችን፣ እናም ምንም እንኳን በመካከላቸው የእስራኤል ደም ቢኖርም፣ አንዳንድ ጊዜ ወንጌሉ የሌላቸው ሀገሮችንም ይጠቁማል። የኋለኛው የቃል ጥቅም በመፅሐፈ ሞርሞንና በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚጠቀሙበት ትርጉም ነው። እስራኤላውያን እስራኤላውያን ያልሆኑትን አያገቡም (አህዛብ), ዘዳግ. ፯፥፩–፫. ጌታ ለአሕዛብም ብርሃን ለመሆን ይመጣል, ኢሳ. ፵፪፥፮. ጴጥሮስ ወንጌሉን ወደ አህዛብ እንዲወስድ ታዘዘ, የሐዋ. ፲፥፱–፵፰. እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ንስሐን ሰጣቸው, የሐዋ. ፲፩፥፲፰. አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን በአንድ ቤተክርስቲያን ተጠምቀናልና, ፩ ቆሮ. ፲፪፥፲፫. በወንጌል አሕዛብ አብረው በክርስቶስ ወራሾች መሆን ይገባቸውል, ኤፌ. ፫፥፮. መፅሐፈ ሞርሞን የተጻፈው በአህዛብ ነው, የመፅሐፈ ሞርሞን ርዕስ ገፅ (ሞር. ፫፥፲፯). ከአህዛብ መካከል አንድ ሰው በብዙ ውኃዎች ላይ ሄደ, ፩ ኔፊ ፲፫፥፲፪. ሌሎች መፅሀፎች ከአህዛብ መጡ, ፩ ኔፊ ፲፫፥፴፱. የወንጌል ሙሉነት ወደ አህዛብ ይመጣል, ፩ ኔፊ ፲፭፥፲፫ (፫ ኔፊ ፲፮፥፯; ት. እና ቃ. ፳፥፱). ይህ ምድር ለአህዛብ የነፃነት ምድር ይሆናል, ፪ ኔፊ ፲፥፲፩. አህዛብ ከወይራ ዛፍ ጋር ይመሳሰላል, ያዕቆ. ፭. ወንጌሉ በአህዛብ ጊዜ ይመጣል, ት. እና ቃ. ፵፭፥፳፰ (ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፯). ቃል እስከ ምድር ዳርቻ፣ መጀመሪያ ወደ አህዛብ፣ እና ከዚያም ወደ አይሁድም ይዞራሉ, ት. እና ቃ. ፺፥፰–፲. ሰባዎቹ ለአህዛብ በሙሉ ልዩ ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፭. መጀመሪያ ወደ አህዛብ እና ከዚያም ወደ አይሁዶች፣ ሁሉንም ሀገሮች እንዲጠሯቸው የቤተክርስቲያኔን ሽማግሌዎች ላኩ, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፰.