የጥናት እርዳታዎች
ሕዝቅኤል


ሕዝቅኤል

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ትንቢተ ሕዝቅኤልን የጻፈው ነቢይ። የሳዶቅ ቤተሰብ ካህን እና በናቡከደነዖር በምርኮ ከተወሰዱት አይሁዳ አንዱ ነበር። ከአይሁዳ ተሰዳጆች ጋር በባቢሎን ሰፈረ እናም ለሀያ ሁለት አመት፣ ከ፭፻፺፪ እስከ ፭፻፸ ም.ዓ. ድረስ፣ ተነበየ።

ትንቢተ ሕዝቅኤል

የሕዝቅኤል ትንቢት በአራት ክፍሎች ለመከፋፈል ይቻላል። ምዕራፍ ፩–፫ ስለ እግዚአብሔር ራዕይና ሕዝቅኤል ለአገልግሎት ስለተጠራበት ይናገራሉ፤ ምዕራፍ ፬–፳፬ በኢየሩሳሌም ላይ ስለነበሩ ፍርዶች እና ለምን እንደተሰጡም ይናገራሉ፤ ምዕራፍ ፳፭–፴፪ በሀግሮች ላይ ፍርዶችን ያውጃሉ፤ እናም ምዕራፍ ፴፫–፵፰ የኋለኛው ቀን እስራኤል ራዕዮችን ይመዘግባሉ።