የጥናት እርዳታዎች
መፅሐፈ መሳፍንት


መፅሐፈ መሳፍንት

የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ። መፅሐፈ መሳፍንት ከኢያሱ ሞት እስከ ሳሙኤል መወለድ ድረስ ስለእስራኤል ይናገራል።

ምዕራፍ ፩–፫ የመፅሐፈ መሳፍንት መቅድም ናቸው። እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ስላላስወጡ (መሳ. ፩፥፲፮–፴፭)፣ እምነት ማጣት፣ ከማያምኑት ጋር መጋባት፣ እና ጣዖት ማምለክ በሆኑት ውጤቶች እስራኤላውያን መሰቃየት እንዳለባቸው ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፬–፭ እስራኤልን ከከነዓናውያን ስላዳኑት የዲቦራና የባርቅ አጋጣሚዎችን ይናገራሉ። ምዕራፍ ፮–፰ ጌታ እስራኤልን ከምድያም ስላዳነው ስለጌዴዎን እምነት የሚያሳድግ አጋጣሚዎች ናቸው። በምዕራፍ ፱–፲፪ ውስጥ፣ ብዙዎቹም እስራኤላውያን በክህደት ላይ እያሉ እና በባእድ ገዢዎች በሚገዙበት ጊዜ፣ የተለያዩ ሰዎች እንደ እስራኤል ዳኛ አገለገሉ። ምዕራፍ ፲፫–፲፮ ስለመጨረሻው ዳኛ ሶምሶን መነሳት እና ውድቀት ይናገራሉ። የመጨረሻው ምዕራፍ፣ ፲፯–፳፩፣ የእስራኤል ኃጢያቶች ጥልቀትን እንደሚገልፅ ተጨማሪ ፅሑፍ ለመመልከት ይቻላል።