የጥናት እርዳታዎች
አርማጌዶን


አርማጌዶን

የአርማጌዶን ስም “የሚጎዶ ተራራ” የሚል ትርጉም ካለው ከእብራውያን ሀር ሚጎዶ መንጭ የመጣ ነው። የሚጎዶ ሸለቆ በኤስድራኤሎን ሜዳ ምስራቃዊ ክፍል ውስጥ፣ ከሰሜን ኢየሩሳሌም ሀምሳ ኪሎ ሜትር አልፎ ያለ ነው፣ እና በብሉይ ኪዳን ጊዜዎች ብዙ በጣም ወሳኝ የሆኑ ጦርነቶች የነበረበት ቦታ ነው። በጌታ ዳግም ምፅዓት ቅርብ ጊዜ የሚመጣው ታላቅ እና የመጨረሻው ጦርነት የአርማጌዶን ጦርነት የሚባልበት ምክንያት በዚያ አካባቢ ስለሚጀምር ነው። (ሕዝ. ፴፱፥፲፩ዘካ. ፲፪–፲፬፣ በልዩም ፲፪፥፲፩ራዕ. ፲፮፥፲፬–፳፩።)