የጥናት እርዳታዎች
ሉቃስ


ሉቃስ

በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሉቃስ ወንጌልና የሐዋርያት ስራ ጸሀፊ እና የጳውሎስ የሚስዮን የጉዞ ጓደኛ ነው። ለግሪክ ወላጆች የተወለደ እና ባለ መድኃኒት ነበር (ቄላ. ፬፥፲፬)። ሉቃስ በደንብ የተማረ ነበር። በጢሮአዳ ከጳውሎስ ጋር ሲገናኝ እራሱን እንደ ሐዋሪያ ጳውሎስ የጉዞ ጓደኛ አስተዋወቀ (የሐዋ. ፲፮፥፲–፲፩)። ጳውሎስ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም በተጓዘበት ጊዜ በፊልጵስዩስ ሉቃስ ከጳውሎስ ጋር ነበር (የሐዋ. ፳፥፮)፣ እናም ወደ ሮሜ እስከሚደርሱ ድረስ አብረው ነበሩ። ጳውሎስ ለሁለተኛ ጊዜ በሮሜዎች በታሰረበት ጊዜ ሉቃስ ከእርሱ ጋር ነበር (፪ ጢሞ. ፬፥፲፩)። በባህል እንደሰማዕት ሞተ ይባላል።

የሉቃስ ወንጌል

ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለስጋዊ አገልግሎቱ በሉቃስ የተጻፈው ታሪክ። የሐዋርያት ስራ መፅሐፍ ከሉቃስ ወንጌል የሚቀጥል ነው። ሉቃስ ኢየሱስን እንደ አይሁዶች እና አህዛብ አዳኝ በማሳየት፣ የኢየሱስ አገልግሎት ታሪክን በግልፅ ጻፈ። ስለኢየሱስ ትምህርቶችና ስለድርጊቶቹም ብዙ ጻፈ። ገብርኤል ዘካርያስን እና ማርያምን ስለጎበኘበት (ሉቃ. ፩)፤ ህጻኑ ኢየሱስን በእረኞች መጎብኝት (ሉቃ. ፪፥፰–፲፰)፤ ኢየሱስ በአስራ ሁለት አመቱ በቤተመቅደስ የነበረበት (ሉቃ. ፪፥፵፩–፶፪)፤ ለሰባዎች ስለተሰጠው ሀላፊነት እና መላክ (ሉቃ. ፲፥፩–፳፬)፤ ስለኢየሱስ ደም እንዳላበው (ሉቃ. ፳፪፥፵፬)፤ በመስቀል ላይ ኢየሱስ ከሌባው ጋር ስለተነጋገረው (ሉቃ. ፳፫፥፴፱–፵፫)፤ እና ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ አሳና ማር ስለመብላቱ (ሉቃ. ፳፬፥፵፪–፵፫) ታሪኮች በሉቃስ ውስጥ ብቻ እናገኛለን።

በሉቃስ ወንጌል ውስጥ የተገለጹትን የአዳኝ ህይወት ድርጊቶች ዝርዝር፣ የወንጌሎች ስምምነትን ተመልከቱ።