የጥናት እርዳታዎች
ግብፅ


ግብፅ

በአፍሪካ በሰሜን ምስራቅ ማዕዘን ውስጥ የምትገኝ ሀገር። አብዛኛው የግብፅ ምድር ዘር የማያፈራ እና ባድማ ናት። በዚያ ከሚኖሩት አብዛኛዎቹ ፰፻፺ ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው በናይል ሸለቆ ውስጥ ይኖራሉ።

የጥንት ግብፅ ሀብታምና የበለጸገች ነበረች። ታላቅ የህዝባዊ ህንጻዎች፣ በተጨማሪም መስኖ፤ ለመከላከያም ጠንካራ ከተማዎች፤ እናም የንጉሳዊ ሀውልቶች፣ በልዩም አሁንም ከአለም ድንቅ ነገሮች መካከል የሆኑት የፒራሚድ መቃብሮችና መቅደሶች ተገንብተው ነበር። ለጊዜም፣ የግብጽ መንግስትም የክህነት ፓትሪያርካዊ ስርዓትን የሚያመሳስል አገዛዝ ነበር (አብር. ፩፥፳፩–፳፯)።