የጥናት እርዳታዎች
ሆሴዕ


ሆሴዕ

በሰሜን የእስራኤል መንግስት ውስጥ በጀሮቦአም ካልዕ ዘመነ መንግስት መጨረሻ አካባቢ የተነበየ የብሉይ ኪዳን ነቢይ። በእስራኤል ኃጢያት ውጤት በሆነው በሀገር መዳከም እና ውድመት ጊዜ ነበር የኖረው።

ትንቢተ ሆሴዕ

የመፅሐፉ መሰረታዊ ጭብጥ መልእክት እግዚአብሔር ለህዝቡ ስላለው ፍቅር ነው። ግሰጻዎቹ ሁሉ የሚመጡት በፍቅር ነው፣ እናም የእስራኤል ዳግም መመለስም በፍቅሩ ምክንያት ነው (ሆሴ. ፪፥፲፱፲፬፥፬)። በማነጻጸርም፣ ሆሴዕ የእስራኤልን ክህደትና ታማኝ አለመሆንን አሳየ። ነገር ግን እግዚአብሔር ስለእስራኤል የመጨረሻ ቤዛነት በጉጉት ይጠብቃል (ሆሴ. ፲፩፥፲፪–፲፬፥፱)።