የጥናት እርዳታዎች
የአብርሐም ቃል ኪዳን


የአብርሐም ቃል ኪዳን

አብርሐም ወንጌልን ተቀበለ እና ወደ ሊቀ ካህነት ተሾመ (ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፬አብር. ፪፥፲፩)፤ የዘለአለማዊነት ቃል ኪዳን ወደሆነው ወደ ሰለስቲያል ጋብቻ ገባ (ት. እና ቃ. ፻፴፩፥፩–፬፻፴፪፥፲፱፣ ፳፱)። አብርሐም የእነዚህ ቃል ኪዳናት በረከቶች ሁሉ ለስጋዊ ዝርያው እንደሚሰጥ የተስፋ ቃል ተሰጠው (ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፱–፴፩አብር. ፪፥፮–፲፩)። እነዚህ ቃል ኪዳናት እና የተስፋ ቃላት አብረው የአብርሐም ቃል ኪዳን ተብለው ይጠራሉ። የዚህ ቃል ኪዳን ዳግሞ መመለስ በመጨረሻው ቀናት ወንጌል ዳግሞ መመለስ ነው፤ በዚህም በኩል የምድር ህዝቦች ሁሉ ተባርከዋል (ገላ. ፫፥፰–፱፣ ፳፱ት. እና ቃ. ፻፲፥፲፪፻፳፬፥፶፰አብር. ፪፥፲–፲፩)።