የጥናት እርዳታዎች
ይሁዳ፣ የያዕቆብ ልጅ


ይሁዳ፣ የያዕቆብ ልጅ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የያዕቆብ እና የልያ አራተኛ ወንድ ልጅ (ዘፍጥ. ፳፱፥፴፭፴፯፥፳፮–፳፯፵፫፥፫፣ ፰፵፬፥፲፮፵፱፥፰)። ያዕቆብ ይሁዳ በያዕቆብ ልጆች መካከል በፍጥረት መሪ እንደሚሆን እና ሴሎ (ኢየሱስ ክርስቶስ) የእርሱ ትውልድ እንደሚሆን ባረከው (ዘፍጥ. ፵፱፥፲)።

የይሁዳ ጎሳ

በከነዓን ከሰፈሩ በኋላ የይሁዳ ጎሳ መሪነትን ወሰደ። የእዚህ ዋና ተፎካካሪ ጎሳ የኤፍሬም ጎሳ ነበር። ሙሴ የይሁዳ ጎሳን ባረከ (ዘዳግ. ፴፫፥፯)። ከሰለሞን ዘመነ መንግስት በኋላ፣ የይሁዳ ጎሳ የይሁዳ መንግስት ሆነ።

የይሁዳ መንግስት

በሮብዓም ዘመነ መንግስት የሰለሞን ግዛቶች ወደ ሁለት መንግስቶች ተሰበሩ፣ ዋና ምክንያቱም በኤፍሬም እና በይሁዳ ጎሳዎች መካከል በነበረው ቅንዓት ነበር። የደቡብ መንግስት፣ ወይም የይሁዳ መንግስት፣ የይሁዳ ጎሳን እና የቢንያም ታላቅ ክፍልን ያጠቃለለ ነበር። ኢየሩሳሌም ዋና ከተማ ነበረች። ከሰሜን መንግስት በላይ ያህዌይን የሚያመልኩ ታማኞች ነበሩ። ይሁዳ ከሰሜን እና ከምስራቅ መጠቃት እስከዚህም የተጋለጡ አልነበሩም፣ እናም እስከባቢሎን ምርኮ ድረስ ዋነኛው ሀይል በዳዊት ቤተሰብ እጆች ውስጥ ነበር። የይሁዳ መንግስት ብዙ ህዝብ ከነበረው እና ጠካራ ከነበረው ከእስራኤል መንግስት ውድቀት በኋላ ለ፻፴፭ አመት ለመኖር ችሏል።

የይሁዳ በትር

ይህም መፅሐፍ ቅዱስን እንደ ይሁዳ ቤት መዝገብ ይጠቁመዋል (ሕዝ. ፴፯፥፲፭–፲፱)። በኋለኛው ቀናት፣ የእስራኤል ቤት ቅርንጫፎች በሚሰበሰቡበት ጊዜ፣ ቅዱስ መዝገቦቻቸውም አብረው ይሰበሰባሉ። እነዚህ የቅዱሣት መጻህፍት መዝገቦች እርስ በራስ ይረዳዳሉ እናም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእስራኤል አምላክ እና የአለም ሁሉ አምላክ እንደሆነ የአንድነት ምስክርን ይሰራሉ፣ (ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፶፥፳፬–፴፮ [ተጨማሪ]፪ ኔፊ ፫፳፱)።