ምዕራፍ ፳፱
ብዙ አህዛብ መፅሐፈ ሞርሞንን አይቀበሉም—ሌላ መፅሐፍ ቅዱስ አያስፈልገንም ይላሉ—ጌታ ለብዙ ሀገሮች ይናገራል—በመጽሐፍት ላይ በሚፃፉት ዓለምን ይፈርዳል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ ነገር ግን እነሆ፣ ከሰው ልጆች ጋር የገባሁትን ሀቃልኪዳኔን አስብ ዘንድ፣ የእስራኤል ቤት የሆኑትን ህዝቤን ደግሜ ለመሰብሰብ ክንዴን ለለሁለተኛ ጊዜ አነሳ ዘንድ፤
፪ እናም ደግሞ ዘርህንም አንደማስታውስ፤ እናም የዘርህ ሀቃል ከአፌ ወደ ዘርህ እንደሚያልፍ፤ ቃሌም የእስራኤል ቤት ለሆኑት ህዝቦቼ ለአርማ ይሆን ዘንድ ወደ ምድር ዳርቻ ሐእንደሚያፏጭ፤ ለአንተ ኔፊና ደግሞ ለአባትህ የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሰው ዘንድ፤ በዚያን ቀን በእነርሱ መካከል መድንቅ ስራን መስራት ስቀጥል፣ ብዙዎች ይኖራሉ—
፫ እናም ቃሎቼ ወደፊት ስለሚያፏጩ—ብዙ አህዛብ እንዲህ ይላሉ፣ ሀመፅሐፍ ቅዱስ! መፅሐፍ ቅዱስ! መፅሐፍ ቅዱስ አለን፣ እናም ሌላ መፅሐፍ ቅዱስ ሊኖር አይችልም።
፬ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ሞኞች ሆይ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ይኖራቸዋል፤ እናም ከእኔ የጥንት የቃል ኪዳን ህዝቦቼ ሀከአይሁዶች ይወጣል። እናም ከአይሁዶች ስለተቀበሉት ለመፅሐፍ ቅዱስ እንዴት አድርገው ያመሰግናሉ? አዎን፣ አህዛብስ ምን ማለታቸው ነው? ችግርን፣ የጉልበት ስራንና፣ የአይሁዶችን ስቃይ፣ እንዲሁም ለአህዛብ ደህንነትን ለማምጣት ለእኔ ያላቸውን ትጋት ያስታውሳሉ?
፭ እናንት አህዛብ ሆይ፣ የጥንት የቃል ኪዳን ህዝቦቼ አይሁዶችን ታስታውሳላችሁ? አታስታውሱም፤ ነገር ግን እናንተ ረግማችኋቸዋልና፣ ሀጠልታችኋቸዋል፣ እናም እነሱን ለመመለስም አልፈለጋችሁም። ነገር ግን እነሆ፣ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በራሳችሁ ላይ አደርጋለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ጌታ ህዝቤን አልረሳሁምና።
፮ እናንት ሞኞች፣ ሀመጽሐፍ ቅዱስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ አለን፣ እናም ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ አንፈልግም የምትሉ። በአይሁዶች ካልሆነ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስን አግኝታችኋልን?
፯ ከአንድ በላይ ሀገር እንዳለ አታውቁምን? እኔ ጌታ አምላካችሁ፣ ሰዎችን ሁሉ ሀእንደፈጠርኩ፣ እናም እኔ በባህር ለደሴቶች ያሉትን እንደማስታውስና በላይ በሰማይ እንዲሁም በታች በምድር እንደምገዛ፣ ለሰው ልጆች ቃሌን፣ አዎን፣ ለሁሉም የምድር ሀገሮችም እንኳን እንደማመጣ አታውቁምን?
፰ ስለዚህ ቃሌን በይበልጥ ስለተቀበላችሁ ታጉረመርማላችሁ? እኔ እግዚአብሔር ስለመሆኔ፣ አንዱን ሀገር እንደሌላኛው እንደማስታውሰው፣ ሀየሁለት ሀገሮች ለምስክርነት ለእናንተ ምስክር መሆኑን አታውቁምን? ስለሆነም፣ ለአንዱ ሀገር እንደተናገርኩት ለሌላኛውም አንድ አይነት ቃል እናገራለሁ። እናም ሁለቱ ሀገሮች ሲገናኙ የሁለቱ ሐሀገሮች ምስክርነትም ደግሞ ይገናኛሉ።
፱ እናም ይህን የማደርገውም ለብዙዎች እኔ ትናንትም፣ ዛሬና ለዘለዓለም ሀአንድ መሆኔን፤ ቃሌንም በፈቃዴ መሰረት እንደምናገር አረጋግጥ ዘንድ ነው። እናም አንድ ለቃል በመናገሬ ሌላ መናገር አይችልም ብላችሁ ትገምታላችሁ፤ ምክንያቱም ስራዬ ገና አላለቀም፤ ወይም ይህ እስከ ሰው ዘር መጨረሻ፣ ከዚያም እስከ ዘለዓለም ድረስ አያልቅም።
፲ ስለሆነም፣ እናንተ መፅሐፍ ቅዱስ ስላላችሁ የእኔን ሀቃል ሁሉ ይዟል ብላችሁ አታስቡ፤ እኔን ሌላም እንዲፃፍ አላደርግም ብላችሁ አታስቡ።
፲፩ በምስራቅና በምዕራብና፣ በሰሜን፣ እናም በደቡብና፣ በባህሩ ደሴት ያሉትን ሰዎች ሀሁሉ እኔ የተናገርኳቸውን ቃላት ሁሉ ለይፅፋ ዘንድ አዛቸዋለሁና፤ ሐበመፅሐፉ ውስጥ በተፃፉትም፣ ማንኛውንም ሰው እንደስራው፣ በተፃፈው መሰረት ዓለምን መእፈርዳለሁ።
፲፪ እነሆም፣ ሀለአይሁዶች እናገራለሁ እናም ይፅፉታል፤ ለኔፋውያንም ደግሞ እናገራለሁ፣ እናም ለይፅፉታል፤ እኔ መርቼ ያወጣኋቸው የእስራኤል ቤት ለሆኑት ለሌሎቹ ነገዶችም ደግሞ እናገራለሁ፣ እናም ይፅፉታል፤ እኔም ሐለሁሉም የምድር ሀገሮችም ደግሞ እናገራለሁ፣ እናም ይፅፉታል።
፲፫ እናም እንዲህ ይሆናል ሀአይሁዶች የኔፋውያን ቃል ይኖራቸዋል፣ ኔፋውያንም የአይሁዶች ቃል ይኖራቸዋል፤ እናም ኔፋውያንና አይሁዶች ለየጠፉት የእስራኤል ነገዶች ቃል ይኖራቸዋል፤ እናም የጠፉት የእስራኤል ነገዶችም የኔፋውያንና የአይሁዶች ቃል ይኖሩዋቸዋል።
፲፬ እናም እንዲህ ይሆናል ሀከእስራኤል ቤት የሆኑት ህዝቤ በርስተ ምድራቸው ይሰበሰባሉ፤ እናም ቃሌም ደግሞ ለበአንድ ይሰበሰባል። ከቃሌና ሐየእስራኤል ቤት ከሆኑት ህዝቤ ጋር የሚጣሉትን፣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔንና፣ ለአብርሃም መለዘለዓለም ሠዘሩን እንደማስታውስ ረቃል መግባቴን አሳያቸዋለሁ።