ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፲፱


ምዕራፍ ፲፱

ኢሳይያስ ስለመሲሁ ተናገረ—በጨለማ ያለ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ያያል—ህፃን ልጅ ተወልዶልናል—እርሱም የሠላም አለቃ ይሆናል በዳዊትም ዙፋን ላይ ይነግሳል—ኢሳይያስ ፱ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ይሁን እንጂ፣ ጭጋግም በጭንቀት በነበረሽ አይነት አይሆንም፣ በመጀመሪያ የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር በቀላል መታ፣ እና በኋላ ግን በዮርዳኖስ በስተጀርባ ያሉትን የገሊላ ሀገሮች በቀይ ባህር አምርሮ መታ።

በጨለማ የሄደ ህዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድርም ለኖሩት ብርሃን ወጣላቸው።

ህዝብህን አብዝተሃል፣ ደስታንም ጨምረሃል—በመከር ደስ እንደሚላቸው፣ እና ምርኮንም ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሰዎች በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

አንተም የሸክሙን ቀንበር፣ የጫንቃውንም በትር፣ የአስጨናቂውንም በትር ሰብረሃልና።

ሁሉም የተዋጊው ጦርነት በሁከት የተሞላ ነውና፣ እናም ልብሶች በደም ተጨማልቀዋል፤ ነገር ግን ይህኛው በመቃጠልና በእሳት ማቃጠያ ይሆናል።

ህፃንም ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ፣ መካሪ፣ ሀያል አምላክየዘለአለም አባትየሠላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከዘለዓለም ድረስ በፍርድና በፅድቅ ያፀናውና ይደግፈው ዘንድ፣ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፣ ለሰላሙም ፍፃሜ አይኖረውም። የሰራዊት ጌታ ቅንዐት ይህንን ያደርጋል።

ጌታ ቃሉን ለያዕቆብ ላከ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።

እናም ሁሉም ህዝብ ኤፍሬምም ቢሆን እንኳ እናም የሰማርያ ሰዎች፣ በትዕቢትና በኩራት እንዲህ የሚሉት ሁሉ ያውቃሉ፤

ጡብ ወድቋል፣ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሰራለን፣ የሾላው ዛፍ ተቆርጦአል፣ ነገር ግን በዝግባ እንተካዋለን።

፲፩ ስለዚህ ጌታ በረአሶን ላይ ጠላቶችን ያስነሳል፣ ጠላቶቹንም በአንድነት ይሰበስባል።

፲፪ ሶርያን ከፊትና ፍልስጤምን ከኋላ፤ እናም እስራኤልን በተከፈተ አፍ ይበሉአታል። በዚህ ሁሉ እንኳን ቁጣው አልበረደችም፣ ነገር ግን አሁንም እጁን እንደዘረጋ ነው።

፲፫ ወደ እርሱ ያልተመለሱት ተመተዋልና፣ የሰራዊት ጌታንም አልፈለጉም።

፲፬ ስለዚህ ጌታ ራስንና ጅራትን፣ ቅርንጫፍና እንግጫን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቆርጣል።

፲፭ ሽማግሌው እርሱ ራስ ነው፣ ሀሰትን የሚያስተምረው ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።

፲፮ የዚህ ህዝብ መሪዎች ህዝቡን እንዲሳሳት ያደርጉታልና፣ እናም ተመሪዎቹ ደግሞ ይጠፋሉ።

፲፯ ሰው ሁሉ ግብዝና ክፉ ሰሪ ነውና፣ አፉም ሁሉ ስንፍናን ይናገራልና፣ ስለዚህ ጌታ በወጣቶቻቸው ደስ አላለውም፣ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶችም ምህረት አይኖረውም። በዚህም ሁሉ እንኳን ቁጣው አልበረደለትም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታለች።

፲፰ ኃጢያት እንደእሳት ትቃጠላለችና፤ ይህም ኩርንችቱንና እሾህንም ትበላለች፣ እና ጥቅጥቅ ያለውንም ጫካ ታቃጥላለች፣ እናም እንደጢስም ወደ ላይ ይነሳሉ።

፲፱ በሰራዊት ጌታ ቁጣ የተነሳ ምድር ትጨልማለች፣ ሰዎች ለእሳቱ እንደማገዶ ይሆናሉ፣ ማንም ሰው ወንድሙን አያድንም።

እና እርሱ በቀኙ እጅ ይመነጭቃልና ይራብማል፤ በግራ እጅም ይበላል አይጠግቡምም፤ እያንዳንዱም የራሱን ክንድ ስጋ ይበላል—

፳፩ ምናሴኤፍሬም፤ እናም ኤፍሬም፣ ምናሴ፤ እነርሱ በአንድነት በይሁዳ ላይ ይነሳሉ። ይህም ሁሉ ተፈፅሞ እንኳን ቁጣው ገና አልበረደችምና፣ ነገር ግን አሁንም እጁ ተዘርግታለች።