ምዕራፍ ፳፪
በአንድ ሺህ ዘመን ሰዎች ሁሉ ጌታን ያወድሳሉ—እርሱም በመካከላቸው ይኖራል—ኢሳይያስ ፲፪ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ—አቤቱ ጌታ፣ አመሰግንሀለሁ፤ በእኔ ብትቆጣም እንኳ ቁጣህን አብርደህልኛል፣ አፅናንተህኛልም።
፪ እነሆ፣ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ ሀአምናለሁ፣ እና አልፈራም፤ ጌታ ለያህዌህ ጥንካሬዬና ዝማሬዬ ነውና፤ ደግሞም እርሱ መድኃኒቴ ሆኖአልና።
፫ ስለዚህ፣ ሀውኃንም ከመዳን ጉድጓዶች በደስታ ትቀዳለህ።
፬ እናም በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ—ጌታን ሀአወድሱ፣ ስሙንም ጥሩ፣ በአህዛብም መካከል ስራውን አውጁ፣ ስሙም ከፍ ያለ እንደሆነ አስታውቁ።
፭ ለጌታ ሀዘምሩ፤ እርሱ ታላቅ ስራን ሰርቶአልና፤ ይህም በምድር ሁሉ ታውቋል።
፮ በፅዮን የምትኖሩ ሁሉ ሀጩሁ፣ እልልም በሉ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤሉ ቅዱስ ታላቅ ነውና።