ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፫


ምዕራፍ ፫

ዮሴፍ በግብፅ በራዕይ ኔፋውያኖችን አየ—ስለጆሴፍ ስሚዝ፣ የኋለኛው ቀን ባለራዕይ፤ እስራኤላውያንን ነፃ ስለሚያወጣው ሙሴ፤ እንዲሁም ስለመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት ተነበየ። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

እናም የመጨረሻ ለተወለድከው ዮሴፍ፣ አሁን እናገርሀለሁ። እኔ በተሰቃየሁበት ምድረበዳ ውስጥ ተወልደሀል፤ አዎን፣ በታላቁ የስቃዬ ዘመን እናትህ ወለደችህ።

እናም ለዘለዓለማዊ ደህንነታችሁ የእስራኤልን ቅዱስ ትዕዛዛት ከጠበቅህ ጌታ ይህንን ታላቅ የተከበረ ምድር ለአንተና ለዘሮችህ፣ ከወንድሞችህ ጋር ርስት ይሆን ዘንድ ጌታ ለአንተ እንዲቀድስልህ እመኝልሃለሁ።

እናም አሁን፣ ዮሴፍ በስቃዬ ዘመን ከምድረበዳ ያወጣሁህ የመጨረሻው ልጄ፣ ጌታ ለዘለዓለም ይባርክህ፣ ዘርህ ሙሉ በሙሉ እንዳይጠፋምና

እነሆም አንተ የእኔ የወገብ ፍሬ ነህ፤ እናም እኔ በምርኮ ወደ ግብፅ የተወሰደው የዮሴፍ ዘር ነኝ። እናም ጌታ ለዮሴፍ የገባቸው ቃል ኪዳን ታላቅ ነበሩ።

ስለሆነም፣ ዮሴፍ በእርግጥ ጊዜአችንን ተመልክቷል። እናም ጌታ እግዚአብሔር ከወገቡም ፍሬ ፃድቃን የሆነ የእስራኤል ቤት ቅርንጫፍን እንደሚያስነሳ ከጌታ የተስፋ ቃል አግኝቷል፤ መሲሁ አይደለም፣ ነገር ግን የተገነጠለው ቅርንጫፍ ቢሆንም በጌታ ኪዳን እንዲታወስ በኋለኛው ቀን መሲሁ ራሱን በመንፈስ ኃይል ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ አዎን ከተደበቀው ጨለማና ምርኮ ወደ ነፃነት እነርሱን ለማምጣት የሚገለጥላቸው ነው።

ዮሴፍ በእውነት እንዲህ ሲል መሰከረ—ባለራዕይን ጌታ አምላኬ ያስነሳል፣ ለወገቤም ፍሬ የተመረጠ ባለራዕይ የሚሆን።

አዎን፣ ዮሴፍ በእውነት እንዲህ ተናገረ፣ ጌታ እንዲህ አለኝ፥ የተመረጠውን ባለራዕይ ከወገብህ ፍሬ አስነሳለሁ፤ እናም እርሱ ከወገብህ ፍሬ መካከል የተከበረ ይሆናል። ከአባቶችህ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ወደማወቅ ለመምጣት፣ ለእነርሱም ታላቅ ጥቅም የሚሆን ስራ ታላቅ ስራን ለዘሮችህ፣ ለወንድሞቹ፣ ይሰራ ዘንድ ትዕዛዝን እሰጠዋለሁ።

እናም እኔ ከማዘው ስራ በስተቀር ሌላ ስራ እንዳይሰራ ትዕዛዛትን እሰጠዋለሁ። እናም በፊቴ ትልቅ አደርገዋለሁ፤ የእኔን ስራ ይሰራልና።

እናም የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እርሱም ህዝቦቼን ነፃ ያወጣቸው ዘንድ አስነሳዋለሁ ብዬ ለእናንተ እንደተናገርኩለት ሙሴ ታላቅ ይሆናል።

እናም ሙሴ ከግብፅ ምድር ህዝቦችህን እንዲያወጣ አስነሳዋለሁ።

፲፩ ነገር ግን ባለራዕይ ከመካከልህ አስነሳለሁ፤ እናም ለእርሱም ለዘርህ ቃሌን ያመጣ ዘንድ፣ እናም ቃሌን ለማምጣት ብቻ ሳይሆን፣ አለ ጌታ፣ ነገር ግን የተሰጣቸውን ቃሌን እስከማሳመን ድረስ ኃይልን እሰጠዋለሁ።

፲፪ ስለሆነም፣ የወገብህ ፍሬዎች ይፅፋሉ፤ እናም የይሁዳ ወገብ ፍሬም ይፅፋሉ፤ እናም የውሸት ትምህርቶች ሀሰት መሆናቸውን ለማስረዳትና ፀብን ለማቆም፣ እንዲሁም በወገብህ ፍሬ መካከል ሰላምን ለመመስረትና፣ በኋለኛው ቀን ለአባቶቻቸው ግንዛቤ፣ እናም ደግሞ ለቃል ኪዳኔ ግንዛቤ እንዲመጡ በወገብህ ፍሬ የተጻፈውና፣ ደግሞ በይሁዳ ፍሬ የተጻፈው በአንድነት ያድጋሉ ይላል ጌታ።

፲፫ እናም ጌታ እንዲህ ይላል፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ እንድትመለሱ ስራዬ በሁሉም ህዝቦቼ መካከል በሚጀመርበት ጊዜ እርሱ ከድካም ይበረታል።

፲፬ እናም ዮሴፍ እንዲህ ሲል ተነበየ—እነሆ፣ ባለራዕዩን ጌታ ይባርከዋል፤ እናም እርሱን ለማጥፋት የሚሞክሩ ይሸነፋሉ፤ የወገቤን ፍሬ በተመለከት ከጌታ ያገኘሁት ይህም ቃል ኪዳን ይፈፀማል። እነሆም፣ ይህ ቃል ኪዳን እንደሚፈፀም እርግጠኛ ነኝ፤

፲፭ እናም ስሙም በእኔ ስም ይጠራል፤ ይህም ከአባቱ ስም ጋር አንድ ይሆናል። እናም እርሱ ልክ እንደእኔ ይሆናል፣ ጌታ በእርሱ እጅ የሚያመጣ ነገር በጌታ ኃይል ህዝቦቼን ወደ ደህንነት የሚያመጣ ይሆናልና።

፲፮ አዎን፣ ዮሴፍ ይህን ተንብዮአል—በሙሴም ቃል ኪዳን እንኳን እርግጠኛ እንደሆንኩ፤ በዚህ ነገር እርግጠኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ጌታ ዘርህን ለዘለዓለም እጠብቃለሁ ብሎኛልና።

፲፯ እናም ጌታ አለ፥ ሙሴን አስነሳለሁ፤ እናም በበትሩ ኃይልን እሰጠዋለሁ፤ እናም መልካም ህጎችን እንዲፅፍ ኃይልን እሰጠዋለሁ። ነገር ግን ብዙ ይናገር ዘንድ አንደበት አልሰጠውም፣ በንግግር ኃያል አላደርገውምና። ነገር ግን በራሴ እጅ ጣት ህጌን እፅፍለታለሁ፤ እናም ቃል አቀባይ እሰጠዋለሁ።

፲፰ እናም ጌታ ደግሞ እንዲህ አለኝ—ለወገብህ ፍሬ ባለራዕይ አስነሳለሁ፤ ቃል ተቀባይም ለእርሱ እሰጠዋለሁ። እናም እኔ፣ እነሆ፣ እኔ የወገብህ ፍሬ ፅሁፎችን ለወገብህ ፍሬ እንዲፅፍ አደርገዋለሁ፤ የወገብህ ፍሬ ተናጋሪ ያውጀዋል።

፲፱ እናም እርሱ የሚፅፋቸው ቃላቶች በእኔ ጥበብ ጠቃሚ ይሆናሉ ብዬ ወደ ወገብህ ፍሬ እንዲሄዱ የወሰንኳቸው ቃላት ናቸው። እናም ይህ የወገብህ ፍሬዎች ከምድር ወጥተው እንደሚጮህ አይነት ይሆናል፤ ምክንያቱም እምነታቸውን አውቃለሁና።

እናም እነርሱ ከምድር ይጮሃሉ፤ አዎን፣ ስለወንድሞቻቸውም እንኳን ንስሀ ይገባሉ። ብዙ ትውልድ በእነርሱ ካለፈም እንኳን በኋላ እናም እንዲህ ይሆናል በቃላቸው ቀላልነት የተነሳ ጩኸታቸው ይወገዳል።

፳፩ በእምነታቸው የተነሳ የወገብህ ፍሬዎች ለሆኑት ለወንድሞቻቸው ቃላቸው ከእኔ አፍ ይወጣሉ፤ እናም ከአባቶችህ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን እስከሚያስታውሱም የቃላቸውን ድካም እንኳን በእምነታቸው አበረታዋለሁ።

፳፪ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ልጄ ዮሴፍ፣ በዚህ ሁኔታ ነበር የጥንቱ አባቴ ትንቢትን የተናገረው።

፳፫ ስለዚህ፣ በዚህ ቃል ኪዳን ምክንያት አንተ ተባርከሃል፤ ዘርህም የመፅሐፉን ቃል ስለሚቀበሉ አይጠፋምና።

፳፬ እናም በእነርሱ መካከል፣ የበለጠ መልካምን የሚያደርግ፣ በቃሉም በተግባሩም፣ በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ በመሆን፣ በታላቅ እምነት፣ አስደናቂ ነገሮችን ለመስራት፣ እናም በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነገርን ለማድረግ፣ ወደ እስራኤል ቤትና፣ ወደ ወንድሞችህ ዘሮች ብዙዎችን ደግሞ የሚመልስ አንድ ኃያል ይነሳል።

፳፭ እናም አሁን፣ ዮሴፍ አንተ የተባረክህ ነህ። እነሆ፣ አንተ ትንሽ ነህ፤ ስለዚህ የወንድምህን የኔፊን ቃል አዳምጥ፣ እናም እኔ ስለአንተ የተናገርኳቸው ቃላት ልክ ባልኩት መሰረት ይሆኑልሃልና። ሊሞት የደረሰውንም የአባትህንም ቃል አስታውስ። አሜን።