ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፳፯


ምዕራፍ ፳፯

ጨለማና ክህደት በመጨረሻው ዘመን ምድርን ይሸፍናታል—መፅሐፈ ሞርሞን ይመጣል—ሶስት ምስክሮች ስለመፅሐፉ ይመሰክራሉ—የተማረው ሰው የታተመውን መጽሐፍ ማንበብ አልችልም ይላል—ጌታ አስደናቂና ድንቅ ስራን ይሰራል—ኢሳይያስ ፳፱ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ነገር ግን እነሆ፣ በመጨረሻ ቀናት ወይም በአህዛብ ቀናት—አዎን፣ እነሆ በዚህ ምድር የሚመጡትና በሌላም ምድር፣ አዎን፣ በአለም ምድሮች ሁሉ ላይ የሚሆኑት የአህዛብን እናም ደግሞ የአይሁዶች ሀገሮች፣ እነሆ፣ በክፋቶችና በሁሉም አይነት እርኩሰቶች ይሰክራሉ—

እናም ያ ቀን ሲመጣ የሰራዊት ጌታ በነጎድጓድ፣ በምድር መናወጥና፣ በታላቅ ሁካታ፣ በአውሎ ነፋስና በወጨፎም፣ እንዲሁም በምትበላም እሳት ነበልባል ይጎበኛቸዋል።

እናም ፅዮንን የሚዋጉ፣ እናም የሚያስጨንቋት ሁሉም ሀገሮች እንደህልምና እንደምሽት ራዕይ ይሆናሉ፤ አዎን፣ ለእነርሱ ተርቦ እንደሚያልም ሰው እንኳን ይሆንላቸዋል፣ እናም እነሆ ይበላል፣ ነገር ግን ይነቃልም ነፍሱ ባዶ ናት፤ ወይም ተጠምቶ እንደሚያልም ሰው ነው፣ እናም እነሆ እርሱ ይጠጣል ነገር ግን ይነቃልም እነሆ የዛለ ነው፣ ነፍሱም አምሮት ይኖረዋል፣ አዎን፣ ከፅዮን ተራራ ጋር የሚዋጋ የሀገሮች ሁሉ ብዛት እንዲህም ይሆናሉ።

እነሆም፣ ክፋትን የምታደርጉ ሁሉ፣ ራሳችሁን ቆጥቡ እናም ተደነቁ፣ ትጮሀላችሁና፤ እናም ታለቅሳላችሁ፤ አዎን፣ እናንተ ትሰክራላችሁ ነገር ግን በወይን አይደለም፣ በሚያሰክር መጠጥ ሳይሆን ትንገዳገዳላችሁ።

እነሆም ጌታ ከባድ የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል። እነሆም ዐይኖቻችሁን ጨፍናችኋል ነቢያትንም ተቃውማችኋል፤ እናም በክፋታችሁ የተነሳ ገዢዎቻችሁንና ባለራዕዮችን ሸፍኖባችኋል።

እናም እንዲህ ይሆናል ጌታ እግዚአብሔር የመፅሐፍን ቃል ያመጣላችኋል፣ እናም እነርሱ የሚያንቀላፉት ቃል ይሆናሉ።

እናም እነሆ መጽሐፉ የታተመ ይሆናል፤ እናም በመጽሐፉም ውስጥ ከዓለም መጀመሪያ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው የእግዚአብሔር ራዕይ ይኖራል።

ስለሆነም፣ በታተሙት ነገሮች የተነሳ፣ የታተሙት ነገሮች በህዝቡ በኃጢያትና በመጥፎነት ጊዜ አይሰጡም። ስለዚህ መጽሐፉ ከእነርሱ ይደበቃል።

ነገር ግን መጽሐፉ ለአንድ ሰው ይሰጣል፣ እናም እርሱ በአፈር ያንቀላፉት ቃል የሆነውን የመጽሐፉን ቃል ይሰጣል፣ እናም እነዚህን ቃላት ለሌሎችም ይሰጣል፤

ነገር ግን የታተሙትን ቃላት እንዲሁም መጽሐፉን አይሰጥም። መጽሐፉ የታተመው በእግዚአብሔር ሀይል በመሆኑ እናም የታተመው ራዕይ እንዲመጣ ዘንድ የጌታ ጊዜ እስከሚደርስ ድረስ በመጽሐፉ ውስጥ ይጠበቃል፤ እነሆም እነርሱ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ያሉትን ነገሮች ይገልፃሉ።

፲፩ እናም የታተሙት የመጽሐፉ ቃላት በሰገነት ላይ የሚነበቡበት ጊዜ ይመጣል፤ እነርሱም በክርስቶስ ኃይል ይነበባሉ፤ እናም በሰዎች ልጆች መካከል የነበሩትና፣ እስከ ዓለም ዳርቻ የሚሆኑት፣ ሁሉም ነገሮች ለሰዎች ልጆች ይገለፃሉ

፲፪ ስለሆነም፣ እኔ ለተናገርኩበት ሰው መጽሐፉ በሚሰጥበት በዚያ ቀን፣ መጽሐፉ ከዓለም ዐይን ይደበቃል፣ በእግዚአብሔር ኃይል፣ ከእርሱ መጽሐፉ ከተሰጠው በተጨማሪ፣ በዚያም ከሶስቱ ካዩት ምስክሮች በስተቀር የማንም ዐይን አያየውም፤ እናም እነርሱ ስለመጽሐፉ እውነታና በውስጡ ስላሉት ነገሮች ይመሰክራሉ።

፲፫ እናም ለሰዎች ልጆች የእርሱን ቃል ምስክርነት ይሰጡ ዘንድ፣ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ከጥቂቶቹ በስተቀር ማንም አያየውም፤ ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የታመኑት ቃላት ከሙታን እንደሆነ ይናገራሉ ብሎአልና።

፲፬ ስለሆነም፣ ጌታ እግዚአብሔር የመጽሐፉን ቃል ለማምጣት ይቀጥላል፤ እናም እርሱ ጠቃሚ ናቸው ብሎ በሚያስባቸው ብዙ ምስክሮቹ አፍ የቃሉን እውነትነት ያረጋግጣል፤ እናም የእግዚአብሔርን ቃል ለማይቀበል ለዚያ ሰው ወዮለት!

፲፭ ነገር ግን እነሆ፣ እንዲህ ይሆናል፣ መጽሐፉን ለሚሰጠው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ያልታተሙትን እነዚህን ቃላት ውሰድና እርሱ ለተማረው እንዲያሳየውና—ይህን እንድታነበውም እለምናለሁ እንዲለው ለሌላው ስጠው። እናም የተማረውም እንዲህ ይላል—መጽሐፉን ወደ እኔ አምጣው አነባቸዋለሁ።

፲፮ እናም አሁን፣ ይህን የሚሉት በአለም ክብር የተነሳና ሀብት ለማግኘት እንጂ ለእግዚአብሔር ክብር አይደለም።

፲፯ እናም ሰውየውም እንዲህ ይላል፥ መጽሐፉን ማምጣት አልችልም፣ ምክንያቱም ታትሟልና።

፲፰ የተማረውም እንዲህ ይላል—ይህንን ለማንበብ አልችልም።

፲፱ ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፣ ጌታ እግዚአብሔር መጽሐፉን እና በዚያም ያሉትን ቃላት በድጋሚ ላልተማረው ይሰጣል፤ እናም ያልተማረው ሰው እንዲህ ይላል—እኔ አልተማርኩም።

ከዚያም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፥ የተማሩት አያነቡአቸውም፣ ምክንያቱም እነርሱ አልተቀበሉትምና፣ እናም እኔ የራሴን ስራ መስራት እችላለሁ፤ ስለዚህ አንተ የምሰጥህን ቃላት አንብባቸው።

፳፩ የታተሙትን ነገሮች አትንካ፣ ምክንያቱም በራሴ ጊዜ አመጣቸዋለሁና፤ ለሰዎች ልጆችም የራሴን ስራ መስራት እንደምችል አሳያቸዋለሁና።

፳፪ ስለሆነም፣ እኔ ያዘዝኩህን ቃላት ስታነብ፣ እናም ቃል የገባሁልህን ምስክርነት ስታገኝ፣ ከዚያም መጽሐፉን በድጋሚ ታትማለህ፣ እናም በራሴ ጥበብ ለሰው ልጆች ሁሉንም ነገሮች መግለጫዬ እስከሚደርስ ያላነበብሃቸውን ቃላት እጠብቀው ዘንድ ለእኔ ትሸሽገዋለህ።

፳፫ እነሆም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እኔም የተአምራት አምላክ ነኝ፤ እናም ለዓለም እኔ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ለዘለዓለም አንድ መሆኔን አሳያለሁ፤ እናም እንደ እምነታቸው ካልሆነ በስተቀር በሰዎች ልጆች መካከል አልሰራም።

፳፬ እናም በድጋሚ እንዲህ ይሆናል፣ የተሰጡትን ቃላት ለሚያነበው ጌታ እንዲህ ይለዋል—

፳፭ ይህ ህዝብ በአፋቸው ወደ እኔ እስከቀረቡ፣ በከንፈሮቻቸውም እስካከበሩኝ፣ ልባቸውን ግን ከእኔ እስካራቁ፣ እናም ወደ እኔ ያላቸው ፍርሀት በሰዎች አስተያየት የተማሩ እስከሆኑ ድረስ

፳፮ ስለዚህ፣ በዚህ ህዝብ መካከል ድንቅ ስራ፣ አዎን፣ ድንቅ ስራ እና አስገራሚ ነገር መስራቴን እቀጥላለሁ፣ የጥበበኞቻቸው እና የተማሯቸው ጥበብ ትጠፋለችና፣ እናም የአስተዋዮቻቸውም ማስተዋል ትሰወራለች።

፳፯ እናም ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለሚሰውሩ ወዮላቸው! ስራቸውም በጨለማ ውስጥ ነው፤ እናም ማን ያየናል፣ ማንስ ያውቀናል? ይላሉ። እናም ደግሞ እንዲህ ይላሉ—በእርግጥ ነገሮችን የምታጣምሙት እንደሸክላ ሰሪ ጭቃ ናቸው። ነገር ግን እነሆ፣ ስራቸውን በሙሉ እንደማውቅ አሳያቸዋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ። ስራ ሰሪውን አልሰራኸኝም ይለዋልን? ወይስ መውጠሪያ የወጠረውን አታስተውልም ይለዋልን?

፳፰ ነገር ግን እነሆ፣ የሰራዊት ጌታ እንዲህ ይላል—ለሰው ልጆች ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ መስክ የሚለወጥበት ጊዜ ረጅም እንደማይሆን አሳያቸዋለሁ፤ እናም ፍሬያማው መስክ እንደጫካ ይመስላል።

፳፱ እናም በዚያ ቀን ደንቆሮዎች የመጽሐፉን ቃል ይሰማሉ፣ እናም የእውሮችም ዐይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ውስጥ ወጥተው ያያሉ።

እናም ደግሞ የዋሆች ይጨምራሉ፣ ደስታቸውም በጌታ ይሆናል፣ እናም በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም በእስራኤሉ ቅዱስ ይደሰታሉ።

፴፩ ጌታ ህያው እንደሆነ አሸባሪዎችም ወደከንቱ እንደሚመጣ ያያሉ፣ የሚያሾፉትም ይጠፋሉ፣ እናም ለክፋት የተዘጋጁ ሁሉ ይቆረጣሉና፤

፴፪ እናም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉም፣ እናም በበርም ለሚገስፀው ወጥመድን የሚያኖሩም፣ ፃድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱም ይቆረጣሉ።

፴፫ ስለዚህ፣ አብርሃምን የተቤዠ ጌታ፣ የያዕቆብን ቤት በተመለከተ እንዲህ ይላል—ያዕቆብ አሁን አያፍርም፣ ፊቱም አሁን አይገረጣም።

፴፬ ነገር ግን በእርሱ መካከል የእጄን ስራ ልጆቹን ባየ ጊዜ፣ ስሜን ይቀድሳሉ፣ እናም የያዕቆብን ቅዱስ ይቀድሳሉ፣ እናም የእስራኤልን አምላክ ይፈራሉ።

፴፭ በመንፈስም ደግሞ የተሳሳቱ ያስተውላሉ፣ እናም የሚያጉረመርሙ ትምህርትን ይማራሉ